
የአማራ ወጣቶች ማህበር የደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ በአጣዬ እና አካባቢው ለሚገኙ የወገን ሀይሎች ከ60 ደርዘን በላይ የሚጠጣ ውሃ ድጋፍ አደረገ ‼️ ጥር 21 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል በሸዋ አጣዬ እና አካባቢው ጀውሃ፣ሸዋሮቢት እንዲሁም አካባቢው በአማራ ልዩ ሀይል ላይ ሆን ተብሎ በተቀነባበረ መልኩ ጥቃት መድረሱና መፈፀሙ የሚታወስ ነው። የአማራ ወጣቶች ማህበርም በደረሰው የወገናችን ሀይል ጉዳት ፣ክህደት ቁጭት ቢሰማውም ፤የአማራ ልዩ ሀይል የደረሰውን ክህደት ለመቀልበስ እና የኦነግ ተላላኪዎችን አስተምሮ ቅጣት ቀጥቶ ለመመለስ በውጊያ ለቆዩ ወንድሞቻችን ፦የአማራ ልዩ ሀይል ፣የአማራ ፋኖ እና ሚኒሻ የአማራ ወጣቶች ማህበር በደብረብረሃን ቅርንጫፍ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ።ከዚህ መካከል ለወገን ጦር ከ60 ደርዘን በላይ የሚጠጣ ውሃ ማቅረብ አንዱ ተግባር ነበር ። በቀጣይም የአማራ ወጣቶች ማህበር በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ከጀግናው የአማራ ልዩ ሀይል ፣የአማራ ፋኖ እና የአማራ ሚሊሻ ጎን መሆናችንን እየገለፅን ለሁለተኛ ዙር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናችንን መግለፅ እንወዳለን። የአማራ ወጣቶች ማህበር ጥር 21/2015 ዓ.ም የተባበረ ክንዳችንን ለአንድ አማራ ‼️ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post