የአማራ ወጣቶች ማህበር ደማችንን ለጀግኖቻችን በሚል የደም ልገሳ ሊያደርግ ነው አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 14/2013 ዓ•ም ባህርዳር ደማችንን ለጀግ…

የአማራ ወጣቶች ማህበር ደማችንን ለጀግኖቻችን በሚል የደም ልገሳ ሊያደርግ ነው አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 14/2013 ዓ•ም ባህርዳር ደማችንን ለጀግኖቻችን፣ህይወቱን ለሰጠን ደማችን እንሰጣለን፡፡በሚል መሪ ቃል በአማራ ወጣቶች ማህበር ማዘጋጀቱን ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል። የአማራ ወጣቶች ማህበር ለወገን ክብር ለሚዋደቅ ጀግና ክብር ይሰጣል። በጭንቅ ቀን ተፈትነው አኩሪ ገድል ለፈፀሙ ጀግኖች፥ የአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ፣ሚሊሻ እና ቀዳሽ-ተኳሽ ለሆነው ህዝባችን የሚሆን የደም ልገሳ ፕሮግራም እሁድ 18/04/13 ዓ.ም በመላው የአማራ ክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ይካሄዳል ሲል ገልፆአል። የአማራ ወጣቶች ማህበር የፊታችን እሁዱ ባዘጋጀው የደም ልገሳ መርሀግብር በአንፀባራቂ ድል ታሪካችን ላደሱ ጀግኖች፣ ደም እንዲለግሱ የእክብሮት ጥሪውን አስተላልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply