የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ማስረከቡን አስታዉቋል፡፡የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአ…

የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ከ21 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ማስረከቡን አስታዉቋል፡፡

የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ከ20 በላይ የሚሆኑ የአማራ ተወላጆች ማህበራት ጥምረት ነዉ፡፡

በዚህ የማህበራት ጥምረት ከዉጭ የሚሰበሰብ ገንዘብን በኢትዮጵያ ሆኖ የሚያስተባብርና በሚገባ ለተጎጅዎች እንዲደርስ የሚሰራ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ተቋቁሞ ነበር፡፡

የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ፤ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በጎንደርና በወሎ የሚገኙ ዜጎች ላይ በህወሃት በተከፈተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ፣ ለተሰደዱና ለተደፈሩ ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ለማድረስ እንዲቻል በአገር ውስጥ ኮሚቴ አቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱን የኮሚቴው ሰብሳቢ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ገልጻለች፡፡

ይሁንና መንግስት በግለሰቦች በኩል የሚደረጉ የእርዳታ ሃብት ማሰባሰብ ሥራዎችን መከልከሉን ተከትሎ ኮሚቴው ሥራ ማቆሙን አስታዉቃለች፡፡

የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ በመላው አለም ከሚገኙ የአማራ ማህበራትና ተወላጆች ሲያሰባስብ ከቆየዉ 24 ሚሊየን 607 ሺህ 774 ብር ውስጥ፤ 21 ሚሊየን 8 ሺህ 724 ብርን ለተለያዩ የእርዳታ ተግባራት ማዋሉን ገልጿል፡፡

ቀሪዉን 3 ሚሊየን 596 ሺህ 50 ብር ወደ ዩቶር የገበሬዎች በጎ አድራጎት በማዛወር በዚህ የበጎ አድራጎት ማህበር በኩል ለተጎጂዎች እንዲደርስ እንደሚደረግም አስታዉቋል፡፡

የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ፣በጎንደር፣በጎጃም፣በሸዋና በደሴ ሲያደርጋቸዉ ከነበሩ የእለት ደራሽ ምግብና አልባሳት ድጋፎች ባሻገር በጋራ ለመስራት ምቹ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተሰባስበዉ እርሻ እንዲጀምሩ ትራክተሮችን የሚያገኙበት አማራጭን እየተከተለ እንደሆነም ተናግሯል፡፡

በአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ በኩል በቀጣይ ሊሰሩ የታቀዱ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸዉ ፕሮግራም መሰረት በዩቶር የገበሬዎች በጎ አድራጎት በኩል መከናወናቸዉን ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡

የአማራ የአስቸኳይ ጊዜ ሃብት አሰባሳቢ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ስራዉን ማቆሙን በይፋ ቢያሳዉቅም በገንዘብ አሰባሰቡ ላይም ሆነ ስርጭቱ ላይ የሚፈጥረዉ ምንም አይነት ችግር እንደማይኖርም ተገልጿል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ

ሚያዚያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply