You are currently viewing የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን የሀዘን መግለጫ ሰጠ።                    አሻራ ሚዲያ        ታህሳስ 16/2013 ዓ•ም ባህርዳር በቤንሻንጉል መተከል ዞን ቡለን ወረ…

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን የሀዘን መግለጫ ሰጠ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 16/2013 ዓ•ም ባህርዳር በቤንሻንጉል መተከል ዞን ቡለን ወረ…

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን የሀዘን መግለጫ ሰጠ። አሻራ ሚዲያ ታህሳስ 16/2013 ዓ•ም ባህርዳር በቤንሻንጉል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን አማሮች ላይ ዘርን መሠረት በአደረገው ዘግናኝ ጭፍጨፋ በተመለከተ መግለጫ ሰቷል።። አገር እንደ አገር እንድትቆም እና እንድትቀጥል ዘረፈ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ ጨዋ ህዝብ በዚህ ደረጃ ግልጽ ጭፍጨፋ ስለተካሄደበት ድርብርብ ጥልቅ ሀዘናችን በድጋሜ እየገለጥን መንግስት እንደመንግስት መንግስታዊ ተግባሩን ባለመወጣቱ ማለትም ተቀዳሚ ተግባሩ የሆነውን የዜጎችን ሠላም እና ደህንነት ማስጠበቅ ባለመቻሉ በየትኛው ደረጃ ያለ የመንግሥት አካል ቅድሚያ ተጠያቂ ሲል (አ ዲ ኅ ን) በመግለጫው ጠቅሷል። በስሙ የተደራጀን የፖለቲካ ፓርቲዎች የምንታገልለት ህዝብ በአገሩ አገር አልባ ሆኖ ዘግናኝ ዕልቂት ሲፈጠምበት መታደግ ካልቻልን የመኖራችን ፋይዳው ከንቱ ነው። በመሆኑም ከመቸውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል በመዘጋጀት የምንችለውን ሁሉ ህጋዊ እና ሠላማዊ የተጠናከረ ሁለገብ ትግል እናካሂዳለንም ብሏል። በመሆኑም መላው የአማራ ሕዝብ ሠላም እና አንድነት ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ በአማራነታቸው ብቻ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከተካሄደባቸው ወንድሞችህ ጋር መቆም የሰውነት ግዴታ መሆኑን በመገንዘብ የምናደርገውን የህልውና ትግል በመቀላቀል በማገዝ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ ሲል ጥሪ አስተላልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply