የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የአዴሃን አመራሮች ህወሃትን በመደምሰስ ወቅት የቆሰሉ ጀግኖችን በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ተገኝተው ጎበኙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ…

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የአዴሃን አመራሮች ህወሃትን በመደምሰስ ወቅት የቆሰሉ ጀግኖችን በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ተገኝተው ጎበኙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ…

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የአዴሃን አመራሮች ህወሃትን በመደምሰስ ወቅት የቆሰሉ ጀግኖችን በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ተገኝተው ጎበኙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ልዩ ሀይል፣የአማራ ፋኖ እና የአማራው ሚሊሻ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በከሃዲው ትሕነግ ላይ በወሰዱት ህግ የማስከበር እርምጃ ከፍተኛ ድል የተመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የአዴሃን አመራሮችም ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም በባህር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል በመገኘት በወቅቱ የቆሰሉ የአማራ ልዩ ሃይል እና የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ጠይቀዋልም። ስለ አገር እና ስለ ህዝብ ሲሉ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉ አባላት የአልባሳትና የምግብ አቅርቦት እጥረት እንዳለባቸው አመራሩ መታዘብ ችሏል ነው ያለው ድርጅቱ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ። በመሆኑም አዴሃን ሲቀጥል የሚመለከተው አካል ይህን በመገንዘብ ከባድ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖች በአስቸኳይ የሚያስፈልጓቸውን ግብአቶች እንዲያሟላ እናሳስባለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply