የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ላይ የተጀመረዉ የተቀናጀ ግድያ ይቁም ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 25…

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ላይ የተጀመረዉ የተቀናጀ ግድያ ይቁም ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25…

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በአማራ ላይ የተጀመረዉ የተቀናጀ ግድያ ይቁም ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ተወላጆች ላይ ማንነትን መሰረት በማድረግ የሚደርሰውን አሰቃቂ ጥቃት መንግስት እንዲያስቆም ሁለት ተቃዋሚ የአማራ የፖለቲካ ድርጅቶች ጠየቁ፤ ለድርጊቶቹም ተጠያቂው መንግስት ነው ብለዋል፤ ብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ የተጋረጠብንን አደጋ ቢረፋፍድም በአጭር ጊዜ ቦታ ቦታውን እንዲይዝ እናደርጋለን ብሏል፡፡ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ( አዴኃን) ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ዛሬ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደተናገሩት በተለያየ ጊዜ በአራቱም አቅጣጫ የአማራ ተወላጆችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች እየደረሱ ነው፡፡ ለዚህም የመንግስት ቸልተኝነትና ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ አቶ ተስፋሁን አያይዘውም “ስለዜጎች ጥቃት ቅድመ ትንበያ በማስቀመጥ ለመንግስት ተደጋጋሚ ጥቆማ ስንሰጥ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ጊዜ ግን የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ያልቻለ መንግስት ነው፣ አሁንም በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተካሄደ ነው፣ ንፁሐን አማሮች ናቸው እየተገደሉ ያሉት ፖለቲከኞች አይደሉም፣ የታጠቁ ወታደሮችም አይደሉም፣ ይልቁንም ህፃናት፣ ሴቶችና ሩጠው ማምለጥ የማይችሉ አዛውንቶች ናቸው እየተገደሉ ያሉት” ብለዋል፡፡ ”ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂው መንግስት ነው” ሲሉ ከሰዋል፡፡ ዋናው መፍትሔ በየአካባቢው ያሉ የአማራ ተወላጆች መደራጀትና ራስን መከላከል ይሆናል፤ ለዚህም እንታገላለን ሲሉ አስርድተዋል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የውጪ ጉዳዮች ኃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተክለማሪያም በበኩላቸው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራው ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎች ስልታዊ በሆነና በተቀናጀ መንገድ የሚከናወኑ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ጉዳዩን ለተለያዩ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ ለዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች፣ ማሳወቃቸውን፣ ከመግለጫ ባለፈ ለመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ችግሩን ተረድተው ግጭቶችና ግድያዎች እንዲያስቆሙ መወትወታቸውንም ገልፀዋል፡፡ እየደረሰ ያለው ግፍ የሰው ልጅ ከሚሸከመው በላይ በመሆኑ ህዝቡ ቅሬታውን በሰላማዊ መንገድ እንዲገልፅ ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራም መንግስት ከልክሏል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ቴዎድሮስ ጉዳዩ ገለልተኛ ወገን እንዲቋቋምና እንዲጣራ፣ ወንጀለኞችም ፍርድ እንዲያገኙ መንግስትን ጠይቀዋል፡፡ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደነበሩበት እንዲመለሱና ጉዳት የደረሰባቸውም ካሳ እንዲያገኙም ጠይቀዋል፡፡ ጉዳዩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈለግም ዶ/ር ቴዎድሮስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአማራ ተወላጆች ላይ ማንነትን ያነጣጠረ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት እንደሚያምን ዛሬ አስታውቋል፡፡ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሐም አለኸኝ ዛሬ እንዳሉት በንፁሀን የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው፡፡ ግን የማታ ማታ ድሉ ለተገፉ ወገኖች ይሆናል ብለዋል፡፡ ”ዛሬ በሕዝባችን ላይ የጠለቀች ፀሐይ ነገ በእነርሱም ላይ ትጠልቃለች፣ በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠበትን አደጋ ቢረፋፍድም በአጭር ጊዜ ቦታ ቦታውን እንዲይዝ እናደርጋለን፣ ከመላው ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እጅና ጓንት በመሆን በትግላችን በቅርብ ለድል እንበቃለን” ነው ያሉት፡፡ በመተከል ዞን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ጉራ ፈርዳ፣ ሰሞኑን ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ጉሊሶ ወረዳ ታጣቂዎች በአደረሱት ጥቃት በርካቶች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፤ ብዙዎች ተፈናቅለዋል ንብረትም ወድሟል፡፡ DW እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply