You are currently viewing የአማራ ጀግኖች አደራ (አጀአ)፣ ዩኬ  የአቋም መግለጫ  ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአቋም መግለጫ :- የአማራ ጀግኖች አደራ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረዉ ደም አ…

የአማራ ጀግኖች አደራ (አጀአ)፣ ዩኬ የአቋም መግለጫ ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአቋም መግለጫ :- የአማራ ጀግኖች አደራ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረዉ ደም አ…

የአማራ ጀግኖች አደራ (አጀአ)፣ ዩኬ የአቋም መግለጫ ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአቋም መግለጫ :- የአማራ ጀግኖች አደራ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረዉ ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲፈታ የተደረገዉን የድርድር ዉጤት እንደ መልካም አጋጣሚ ያየዋል። ነገር ግን ድርድሩ የአማራ ህዝብ አንኳር ጥያቄ የሆኑትን የአማራ አጽመ ርስቶች ማለትም ወልቃይትና ራያን ግልጽ በሆነ መንገድ በአማራ አስተዳደር ስር እንዲተዳደሩ ያላስቀመጠና ያልቋጨ በመሆኑ ይህ ድርድር ዘለቄታዊ ሰላም በአገራችን ያመጣል ብለን አናምንም። በተጨማሪም በድርድሩ የማስፈጽሚያ ሰነድ አንቀጽ 10 ቁጥር 4 ላይ እንድተቀመጠዉ የማንነት ጥያቄ ያለባቸዉ የወሰን ጥያቄዎች በህገ መንግስቱ መሰረት ዉሳኔ ያገኛሉ ተብሎ መቀመጡ አሁንም የአማራን አጽመ ርስቶች መልሶ ለወራሪዎች ለመስጠት የታቀደበት መሆኑን ያመላክታል። በመሆኑም የአማራ ህዝብ በግልጽ ሊያዉቀዉ የሚገባዉን ዋና ጉዳይ እንደዚህ ተሸፋፍኖ እንዲመጣ መደረጉ በቀጣይ አደገኛ መዘዝ የሚያመጣ ጉዳይ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በዚህ ድርድር ስምምነት ላይ በተደረሱባቸዉ ዝርዝር ነጥቦች እንደሚታየዉ የትህነግ/ህወሃት ወራሪ ቡድን ላደረሰዉ የአገር ክህደት እና የጦር ወንጀል እንዲሁም በአማራ ህዝብ ላይ ላደረሰዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ከተጠያቂነት ነጻ የሚያድርጉ ናቸዉ። በቀጣይነትም ትህነግ/ህወሃት ራሱን በአዲስ መልክ እንዲያደራጅ ታስቦ በትግራይ በሚቋቋመዉ ጊዚያዊ አስተዳደር ዉስጥ ዋና ተዋናይ እንደሚሆን ስምምነቱ ላይ ተቀምጧል። በመሆኑም በደቡብ አፍሪካ የተካሄደዉ የሰላም ድርድር ለአማራ ህዝብ ከዚህ በፊት ለንደን ላይ ከተደረገዉ አማራን በጠላትነት ከፈረጁ ቡድኖች የተለየ ዉጤት የማያመጣ በመሆኑ የአማራን ህዝብ ዘላቂ ህልዉና ለማስጠበቅ እንዲቻል የአማራ ጀግኖች አደራ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎች አዉጥቷል። 1. ከ30 ዓመታት በላይ በሃይል ተወስደዉ የነበሩ የአማራ አጽመ ርስቶች ወልቃይት ጸለምት እና ራያ አማራ ባልተወከለበትና ባላጸደቀዉ ሀገ መንግስት አማካኝነት እዉነተኛ ፍትህ ያገኛሉ ብለን ስለማንጠብቅ ያለምንም ቅድመ ድርድርና ሁኔታ በአማራ አስተዳደር ስር ሆነዉ እንዲቀጥሉ አስቸኳይ ዉሳኔ እንዲሰጥበት እንጠይቃለን 2. መላዉ የአማራ ህዝብ በሃይል ተወስደዉ የነበሩትን የአማራ አጽመ ርስቶች (ወልቃይት፣ ጸለምት እና ራያ) በሃይልህ ያስመለስህ ስለሆነ ባላጸደቅሀዉ ህገ መንግስት አማካኝነት እንዳይነጥቁህ በንቃት ርስቶችህን እንድትጠብቃቸዉ እናሳስባለን 3. ወራሪዉ ቡድን የከፈተዉን ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገዉ ትግል የተደራጁ የአማራ ፋኖ አባልት፤ ለአማራ የህልዉና ትግል የሚሰሩ የማህበረሰብ አንቂዎች እና የአማራ ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ እንጠይቃለን 4. የአማራ ህዝብ በወራሪዉ ለደረሰበት የመሰረተ ልማት እና ሃብት ንብረት ዉድመት ተገቢዉ ካሳ እንዲፈጸምለት እና መሰረተ ልማቶቹ በልዩ ፕሮጀክት ተይዘዉ በአስቸኳይ እንዲገነቡ እንጠይቃለን 5. ወራሪዉ ቡድን የከፈተዉን ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገዉ ትግል ህይወታቸዉ ያለፉ የአማራ ጀግኖች ቤተሰቦች ተገቢዉን ካሳ በአስቸኳይ እንዲያገኙና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ እንጠይቃለን 6. ወራሪዉ ቡድን የከፈተዉን ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገዉ ትግል የአካል ጉዳት ለደረሰባቸዉ የአማራ ጀግኖች ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፈላቸዉ እና የስራ እድል እንዲፈጠርላቸዉ እንጠይቃለን 7. በመላዉ ዓለም የምንገኝ የአማራ ድርጅቶች ተደረገ የተባለዉ ድርድር ወደፊት የአማራን ህዝብ ለተጠላለፈ ዳግም ባርነት እንዳይዳርገዉ አስቀድመን ዝርዝር አፈጻጸሙን በመከታተል ህዝባችንን ለማንቃትና ለማደራጀት የድርሻችንን ለመወጣት በአንድነት እንድንቆም እንጠይቃለን አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ! የአማራ ጀግኖች አደራ፣ ለንደን፣ ዩናይትድ ኪንግደም ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24 Facebook (https://www.facebook.com/asharamedia24/)Ashara Media – አሻራ ሚዲያ Ashara Media – አሻራ ሚዲያ, Bahir Dar. 216,299 likes · 30,788 talking about this. የህዝብ ድምፅ! Facebook (https://www.facebook.com/asharamedia24/) Ashara Media – አሻራ ሚዲያ Ashara Media – አሻራ ሚዲያ, Bahir Dar. 216,299 likes · 30,788 talking about this. የህዝብ ድምፅ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply