You are currently viewing #የአማራ ፋኖዎች በሽዋ የይፍት ፋኖ አመራሮች  በግፍ ከታሰሩ 6 ወራቶች ቢቆጠሩም አሁንም ድረስ ፍትህ አላገኙም ተባለ! ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፋኖዎቹ  በተደጋጋሚ ፍ/ቤ…

#የአማራ ፋኖዎች በሽዋ የይፍት ፋኖ አመራሮች በግፍ ከታሰሩ 6 ወራቶች ቢቆጠሩም አሁንም ድረስ ፍትህ አላገኙም ተባለ! ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፋኖዎቹ በተደጋጋሚ ፍ/ቤ…

#የአማራ ፋኖዎች በሽዋ የይፍት ፋኖ አመራሮች በግፍ ከታሰሩ 6 ወራቶች ቢቆጠሩም አሁንም ድረስ ፍትህ አላገኙም ተባለ! ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ፋኖዎቹ በተደጋጋሚ ፍ/ቤት ቢቀርቡም ምንም አይነት ፍትህ ሊያገኙ አልቻሉም።እነዚህ ጀግና ወንድሞቻችን ወንጀለኛ አይደሉም የታሠሩበት መንገድም ህገወጥ ነው ሲሉ ምንጮቻችን ለአሻራ ሚድያ ተናግረዋል። መንግስት ሃገርን ከጥፋት የታደጉ የህዝብ ልጆች እያሰረና እያወከበ በተቃራኒው ደግሞ ለወንጀለኞች ጥላ ከለላ ሲሆን ይታያል።ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ ከመንግስት ፍትህ መጠበቅ የለበትም። ተባብረን ጀግኖቻችንን ልናስፈታ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል። እነዚህ ጀግና ፋኖዎች በህልውና ዘመቻው የመንግስትን ጥሪ ተቀብለው ከሌሎች የአማራ ፋኖዎች እና የአማራ ልዩሃይል ጓዶቻቸው ጋር በመሆን ህዝብን እና ሃገርን ከጥፍት የታደጉ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው ሲሉም ጠቁመዋል። በክልላችን ውስጥ እና በሌሎች አካባቢዎች ታስረው የሚገኙ የአማራ ልዩ ሃይል እና የአማራ ፋኖዎቻችን ሁሉም በሚባል ደረጃ ወንጀለኛ ሁነው ሳይሆን የታሰሩት በሴራነው ብለዋል። ስለሆኑም የአማራ ፋኖ በሽዋ የይፋት አመራሮች ካለምንም ፍትህ ከታሰሩ 6 ወራትን ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ ምንም ፍትህ አልተሰጣቸውም። ፖሊስ ምንም አይነት የወንጀል ማስረጃ ባለማግኘቱ ክስ ያልተመሰረተባቸው በመሆኑ በአገዛዙ ይሁንታ ታስረው እየተሰቃዩ የሚገኙትን ፋኖቻችንን ሁላችንም ድምፅ በመሆን ልናስፈታቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24 ፎቶ ከፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply