የአማራ ፋኖ በመርሐቤቴ ፌጥራ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለ3ተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የፋኖ ወታደሮች አስመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በ…

የአማራ ፋኖ በመርሐቤቴ ፌጥራ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለ3ተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የፋኖ ወታደሮች አስመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ሸዋ ዞን በመርሐቤቴ ፌጥራ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለ3ተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ወታደሮች የወረዳው አመራር ተወካዮች ጥሪ በተደረገላቸው የከተማው ነዋሪዎች የመሬ ፋኖ አመራሮች በተገኘበት ታህሳስ 24ቀን 2014 ዓ.ም አስመርቋል። በፕሮግራሙ የታደሙ የመሬ ፋኖ አመራር ፋኖ ዳዊት ቀጸላ በመግቢያ ንግግራቸው ሀገርን በማዳን ጉዞ ላይ የነበራችሁና ራሳቸውን ብቁ አድርጋችሁ ለሰለጠናችሁ የፋኖ አባላት እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል። የዚች ሀገር የመኖርና ያለ መኖር ምስጢር ፋኖ ነው ብንል ማጋነን አይሆንብንም የፋኖ ደሙ ውሀ ሆኖ፣ ስጋው ጭቃ ሆኖ፣ አጥንቱ ድንጋይ ሆኖ ፣ስሮቹን አጥር አድርጎ ፣በሞቱ አገርን የሰራ ድንቅ ፍጥረት ነው ብለዋል። አክለውም በህይወቱ ሀገርን የጠበቀ ጀግና በመሆኑ ዛሬም የተመረቃችሁ የፋኖ አባላቶች የአባቶቻችንን አደራ ተቀብላችሁ ሀገርን የምታስቀጥሉና ትውልድን ከጠላት የምታድኑ እንድትሆኑ የቀደሙት የጀግኖች አባቶቻችን አደራ አለባችሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሀሳብ አስተያየት ከሰጡ አስመራቂዎች መካከል የፌጥራ ፋኖ ተወካይ እንጂነር እዮብ ለማ ፣በመርሐቤቴ ፌጥራ ማሰልጠኛ ጣቢያ አሰልጣኝ አስር አለቃ ጌታባለው ጉሌ ፣ የመርሐቤቴ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ኮማደር ዘለቀው አይዳኙህም ፣ የመርሐቤቴ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ተወካይ እና ወጣት ሊግ አደረጃጀት ወ/ሮ ስመኝ ስንለው ፣ ዘማሪ ዲያቆን ሽፈራው ጌትዬ እና ሌሎች ተሳታፊዎች ይህ ስልጠና በመደረጉና የፋኖ ሰልጣኞች በመመረቃቸው መደሰታቸውን ገልፀው ፋኖ ማለት ንቃተ ህሊናውን የጠበቀ፣ በስነልቦና የተገነባ፣ በቃልኪዳን የተሳሰረ፣ ከራሱ አልፎ ለሌሎቻችን በችግራችን እና በመከራ ጊዜ የሚደርስ የቀደምት የአባቶቹ ልጆች ነው ብለዋል። አንድነታችንን አጠናክረን ከፋኖ ጎን በመቆም ሀገራችንን መጠበቅና ህዝባችንን ከጠላት ወረራ ማዳን አለብን ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ከሰሜን ሸዋ አስተዳደር ገጽ የተገኘ

Source: Link to the Post

Leave a Reply