
የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በጋሸና ግንባር ታላቅ መስዕዋትነት የከፈሉበትን ጓዶቻቸውን አንደኛ ዓመት የሰማዕታት መታሰቢያ ጧፍ በማብራት አስበው ውለዋል ‼️ ሕዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ጀግና አባላት አሸባሪው የህውሀት ሀይል የአማራ ህዝብ ለማዋረድ ፣ አንገት ለማስደፋት እና አገራችን ለማፈራረስ አልሞ ጦርነት በመክፈቱ ፤ ይህንን ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገ ጦርነት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገ የአማራ ፋኖ ስብስብ ነው ። የአማራ ፋኖ በባህር ዳር በጋሸና ግንባር ተሰልፎ ጠላት አይሰበርም ብሎ የተማመነበትን የአርቢት ምሽግ ለመደርመስ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍሏል ።በተከፈለው የከበረ መስዕዋትነት 17 ጓዶቻችን ቁስለኛ ሲሆኑ ፤3 ጓዶቻችን የህይወት መስዕዋትነት ከፍለዋል ። የህይወት መሰዋዕትነትን የከፈሉት የሚከተሉት ናቸው ፦ 1).ፋኖ ማንደፍሮ አድማሱ 2).ፋኖ ሙሉቀን አዳነ 3).ፋኖ አሰናቀው ንጋቱ ናቸው ። በዛሬው ዕለትም የአንደኛ የመስዋዕትነት መታሰቢያውን የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ፣የተሰው ጓዶቻችቸውን ቤተሰቦች በተገኙበት በጧፍ ማብራት ዘክረዋል ። ከዚህ በተጨማሪ በአቃስታ ግንባር ጠላትን ረፍርፎ በክብር በጀግንነት ሰማዕትነትን የተቀበለው ፋኖ አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉንም መቼም አንረሳውምብለዋል ። የከፋላችሁት ታላቅ መሰዋዕትነት አማራ አንገቱ ቀና አድርጎ እንዲሄድ አድርጋችኃል ።ለተከፈለው መስዕዋትነት ልባዊ ክብር አለን ። ትግላችን አልተቋጨም ። ትግላችን ይቀጥላል ።የትግላችን መዳረሻ የአማራ ህዝብ ነፃነት ነው ። አርበኝነት አማራዊ ውርሳችን ፤ፋኖነት ከአባቶቻችን የወረሰነው ታላቁ እሴታችን ነው ‼️ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post