የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ወልደጊዮርጊስ መኮንን፣ ፋኖ ይገርማል በላይ እንዲሁም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ አባል እና ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን ጨምሮ ሌሎችም የግፍ እስረኞች ፍ/ቤ…

የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ወልደጊዮርጊስ መኮንን፣ ፋኖ ይገርማል በላይ እንዲሁም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ አባል እና ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን ጨምሮ ሌሎችም የግፍ እስረኞች ፍ/ቤት ይቀርባሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሃሰት የተወነጀሉት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት የሆኑት ወልደጊዮርጊስ መኮንን ፣ ፋኖ ይገርማል በላይ እንዲሁም የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ አባል እና ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ከሌሎች ንፁሃን የግፍ እስረኞች ጋር ሀምሌ 12/2014 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባሉ። ይህን ተከትሎም የአማራ ፋኖ በባህር ዳር የባህር ዳር እና የአካባቢው ነዋሪዎች በግፍ እስር ላይ ለሚገኙ ወገኖች አጋርነቱንና አብሮነቱን እንዲገልጽ ጥሪ አድርጓል። ሀምሌ 8/2014 ችሎት ለቀረቡ ጀግኖች የባህር ዳር ወጣቶች ፍፁም አጋርነት ፣አንድነት እና አማራዊ ወንድማማችነት አጉልተው ማሳየታቸውን በማውሳት አመስግኗል፤ በነገው እለትም እንዲደገም የከበረ ጥሪውን አስተላልፏል። ከጠዋቱ 2:00 ሰዓተ ጀምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመገኘት ለጀግኖች የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ወንድሞች አብሮነትህ ፣የሞራል ድጋፍ እና ፍፁም አንድነትህን እንድታሳይ በአክብሮት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ጥሪው ያቀርባል ነው ያለው። “ፋኖነት ወንጀል አይደለም፤ ፋኖነት ከቀደምት አባቶቻችን በደም ውርስ የተቀበለነው ፣የክብር ፣የነፃነት የአይበገሬነት መንፈስ ከላይ ሲወርድ ሲዋረድ የተረከብነው መጠሪያችን ነው” ሲል ገልጾታል። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ነፃነት ነው!!ለ

Source: Link to the Post

Leave a Reply