የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ያስተላለፈው አሰቸኳይ ጥሪ‼️ ~~~ ነገ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንገኝ ። በሁለተኛው መዝገብ በሃሰት የተወነጀሉት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር…

የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ያስተላለፈው አሰቸኳይ ጥሪ‼️ ~~~ ነገ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት እንገኝ ። በሁለተኛው መዝገብ በሃሰት የተወነጀሉት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ፋኖ ወልደጊዮርጊስ መኮንን(ራፐር) ፣ፋኖ ይገርማል በላይ (2 pack) ፣ የባልደራስ ለእውነተኘ ዲሞክራሲ አባልና ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው እና እና ሌሎች ንፁሃን ወንድሞቻችን በነገው ዕለት የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይቀርባሉ ። በመሆኑም ባለፈው አርብ በመጀመሪያው የክስ መዝገብ ለሚገኙ ለሁሉም የአማራ ፋኖዎች ያደረጋችሁትን ፍፁም አጋርነት ፣አንድነት እና አማራዊ ወንድማማችነት ነገ ፍ/ቤት ለሚቀርቡ ወንድሞቻችን ትደግሙት ዘንድ የአማራ ፋኖ በባህር ዳር የከበረ ጥሪውን ያስተላልፋል ።ስለሆነም መላው የአማራ ፋኖ በባህር ዳር አባላት ፣የከተማችን ጀግና ወጣቶች እና መላው የከተማችን ነዋሪዎች ነገ ከጠዋቱ 2:00 ሰዐተ ጀምሮ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመገኘት ለጀግኖች የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ወንድሞች አብሮነትህ ፣የሞራል ድጋፍ እና ፍፁም አንድነትህን እንድታሳይ በአክብሮት የአማራ ፋኖ በባህር ዳር ጥሪው ያቀርባል ። ፋኖነት ወንጀል አይደለም ።ፋኖነት ከቀደምት አባቶቻችን በደም ውርስ የተቀበለነው ፣የክብር ፣የነፃነት የአይበገሬነት መንፈስ ከላይ ሲወርድ ሲዋረድ የተረከብነው መጠሪያችን ነው ። የትግላችን መዳረሻ የአማራ ነፃነት ነው‼️

Source: Link to the Post

Leave a Reply