የአማራ ፋኖ በአንድ መዋሃዱን ያስታወቀው የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት በምስረታው እና በወቅታዊ አማራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕ…

የአማራ ፋኖ በአንድ መዋሃዱን ያስታወቀው የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት በምስረታው እና በወቅታዊ አማራዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት በሰጠው መግለጫ ከሽዋ፣ከጎንደር፣ከወሎ እና ከጎጃም ከ4ቱም ማዘናት የተውጣጡ የፋኖ ተወካዮች በተገኙበት ምስረታው መከናወኑን አስታውቋል። የአማራ ፋኖ አንድነት ከብዙ ድካም በኋላ በጎንደር ክፍለ ሀገር ህዳር 13/2015 ዓ/ም ሊመሰረት መቻሉን ነው ም/ቤቱ የገለጸው። በምስረታው እለት የተገኙት ሻለቃ ሰፈር መለሰ አማራ ፋኖን አንድ ለማድረግ ከተለያዩ አካባቢዎች የተገኙ ፋኖዎችን አመስግነው አንድነት አተን ብዙ ውርደት እና መከራ ደርሶብናል፤ ብዙ መስዋዕትነት ከፍለናል አንድነት ሃይል ነው፤ አንድ ከሆን የሚደፍረን አይኖርም ማለታቸው ተገልጧል። ህወሓት ከተረኛው ስርዓት ጋር በመተባበር ወልቃይት እና ራያን ለመውሰድ መሞከሩ የማይቀር ነው ያሉት ሻለቃ ሰፈር ነገር ግን በዚህ ጉዳይ መንግስትም የሚደፈር አይመስለኝም ብለዋል፤ እኛ በህይወት እያለን ግን መሬቻችንን አሳልፈን አንሰጥም ሲሉም ተናግረዋል። የምስራቅ አማራ ፋኖ በጦርነቱ ያስመዘገበውን ድል በማውሳት ምስጋናም አቅርበዋል። ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ በበኩላቸው ጦርነቱን ያሸነፈው የአማራ ፋኖ ነው አማራው ደሞዝ ሳይከፈለው በሬውን ሽጦ እራሱን አስታጥቅ ዘምቶ ባሸነፈው ጦርነት የፌደራል መንግስት እና ህወሓት አማራን በማግለል በአማራ ላይ ተደራድረዋል፤ ትጥቅ እፈታለሁ ያለው ህወሓትም ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል። “ገዢው መንግስት የአማራ ፋኖን ይዘልፋል፤ ጠላታችን ትህነግም ፋኖን ይፈርጃል፤ እንሆ በዚህ ሰአት እንኳን በጋራ እያጠቁን ይገኛሉ” ብሏል ም/ቤቱ በመግለጫው። የአማራ ህዝብ በዚህ ጦርነት ከየትኛውም ክልል በበለጠ ሞቷል፣ወድሟል፣ተጎሳቅሏል በማለት የለፈለውን መስዋዕትነት ያወሳው የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት በሚያሳዝን ሁኔታ ግን በድርድሩ አልተወከለም፤ ህዝባችን እንደ ህዝብ አልተሳተፈም ነው ያለው። እነ ብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፣ ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ እና አቶ ቴወድሮስ ትርፌ አማራ ውክልና ያስፈልገዋል በማለት በተሳታፊ ሲቪክ ድርጅቶች ተመርጠው በተደራዳሪነት መቅረባቸውን እንደሚደግፍ የገለጸው ም/ቤቱ ነገር ግን ከመከላከያው እና ከልዩ ሃይሉ ጋር እኩል ተሰልፈን ዋጋ እንደመክፈላችን መጠን እንደ ፋኖ በድርድሩ ልንወከል ይገባል የሚል ቁርጥ አቋም መያዙንም አስታውቋል። ከዚህ ውጪ በሆነ መንገድ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር እየተደራደረ ያለው መንግስት ፋኖን ትጥቅ እናስፈታለን ማለት ግን ከአሸባሪዎች ጋር በአቻነት እያቀረቡ ፖለቲካ ሰርተን እናተርፋለን ማለት ኢየሱስ ክርስቶስን እና በርባንን እንደማወዳደር ይቆጠራል ሲል ገልጧል። በመጨረሻም የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት አመራሮቹን በመረጠበት እና ባጸደቀበት እለት የሚከተሉትን ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። 1) ም/ቤቱ ከአሁን ቀደም በህወሓት በህገ መንግስታዊ ውሳኔ ሳይሆን በጉልበት በተወሰዱት ወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምት እና ራያ ፈፅሞ የማንደራደርባቸው ቀይ መሰመሮች መሆናቸውን፣ 2) ፋኖን ትጥቁን ለማስፈታትእና ለመበተን የሚሞክር ሃይል “የአማራን ህዝብ እጁን አስረን ለጠላት እንስጥ” ከሚል የመነጨ መሆኑን እንደፋኖ እንረዳለን በመሆኑም ይህ ሊተገበር ቀርቶ ሊታሰብ የማይገባ ቀይ መስመር መሆኑን አበክረን ከወዲሁ እንገልፃለን። 3) በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረው በአማራው ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት በተለይም ላለፉት 4 ዓመታት በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ መሆኑን የገለጸው ም/ቤት ይህም በአንዳንድ በመንግስታዊ መዋቅሩ ውስጥ ባሉ አመራሮች ጭምር እንደሚደገፍ እናምናለን ሲል አክሏል። 4) ለሀገራቸው ዋጋ በከፈሉ ሽልማት ሲገባቸው የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ጋዜጠኞችና ፋኖዎች እንደነ አርበኛ የአማራ ምልክት የሆኑ ዘመነ ካሴ ዓይነት እስረኞች እንዲፈቱ በጥብቅ እንጠይቃለን። 5) በሃገራችን ድርድሩና ምክክሩ ብርጋዴየር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ዶ/ር ወንዶሰን አስፋውና አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ ህዝባዊ ቅቡልነት እንዳላቸው በማመን እንደ ፋኖ በድርድሩ ውስጥ ሊካተቱ እንደሚገባ ጥሪ አድርጓል። 6) የአማራ ፋኖ ለከፈለው መስዋዕትነት እውቅና ሊሰጠው እንደሚገባም እናምናለን ብሏል። 7) በአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት አልተጠቃለልነም ከሚሉ አካላት ጋርም ተቀራርበን ለመስራትና ለአማራ ያገባናል ከሚሉት ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናቸውም ተገልጧል። 8 የአማራን ክልል ለመበተንና ለማፈራረስ የሚሰራ ህዝባችንን ከግዙፍ ማንነት ወደ ህዳጣን ለማውረድ የሚሰራ የፖለቲካ ሴራን ፈፅሞ እንደማንታገስ፣ 9) የተወላገደ አማርኛ የሚናገር አማራ የለም የተወላገደ ህገ መንግስት ልጫንብህ የሚል እና እኛ እንወቅልህ በሚል አማራ ጠል ትርክት በመፍጠር የአማራን ህዝብ ለመከፍፈል የሚሰራ መንግስታዊ አሻጥርን በጥብቅ እንቃወማለን ብሏል። 10) የተከበርከው የአማራ ህዝብ ሆይ: ዛሬ የመሰረትነው የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ዋና አላማው የአማራን ህዝብ እንግልት፣ሰቆቃ፣ሞትና ስደት ለመቀልበስ ብርቱ ህብረት የአማራ መዳኛ እንደሚሆን የአማራን ህዝብ ለማዳን ቤቴ ፣ልጄ፣ሚስቴ ሳንል ዱር ቤቴ ድንጋይ ትራሴ ብለን መዳኛህን በአንድ ዕዝ መስርተናል። ለዚህም እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በመንግስት በኩል የሚፈፀመውን ወከባና ማሳደድ ከፋኖ ጎን በመቆም ለፋኖውም ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ምሽጋችን፣ ጫካችን፣ ትጥቃችን ስንቃችን እና መሳሪያችን ስለሆናችሁ ፋኖን ከተኩላዎች እንድትጠብቁ በአማራ ፋኖ አንድነት ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብሏል። ፋኖነት በክብር የሚኖር፣ የሚኖርበት የክብር ሰገነት፣የብረት ምሰሶ የአማራነት ራስ ነው። የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ምስረታ ጎንደር 13/2015 ዓ/ም። ምንጭ_አሻራ ሚዲያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply