You are currently viewing የአማራ ፋኖ በይፋት (ማጀቴ) ኮማንዶዎችን የባልደራስ አመራሮች ባሉበት እያስመረቀ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ  የአማራ ፋኖ…

የአማራ ፋኖ በይፋት (ማጀቴ) ኮማንዶዎችን የባልደራስ አመራሮች ባሉበት እያስመረቀ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ…

የአማራ ፋኖ በይፋት (ማጀቴ) ኮማንዶዎችን የባልደራስ አመራሮች ባሉበት እያስመረቀ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ በይፋት (ማጀቴ) ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በማጀቴ የፋኖ መሪ የሆኑት ፈለቀ ሙላቱ እና የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በክብር እንግድነት በተገኙበት እያስመረቀ ነው። በእለተ እሁድ የካቲት 20 ቀን 2014 ዓ.ም. እየተመረቁ ያሉት የፋኖ ኮማንዶዎች የሰለጠኑት በፌዴራል ሰራዊት ውስጥ የኮማንዶ አሰልጣኝ በነበሩት አብዮት ወርቁ፣ እንዲሁም ቀደም ብለው በፋኖ ውስጥ የኮማንዶ ስልጠና በሰለጠኑት ማርቆስ ዘነበ እና ሙሉጌታ ሽቶ ነው። መደበኛ ወታደራዊ ስልጠናውን ደግሞ እንግዳ አዘነ፣ እሸቱ ቸርነት፣ ስመኝ መሸሻ አሰልጥነዋል። ፋኖዎች በኮማንዶ ደረጃ መሰልጠናቸው የኢትዮጵያ ጥምር የጦር ሃይልን ወደ ከፍተኛ ብቃት ያደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የባልደራስ ሚዲያ ክፍል ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply