You are currently viewing የአማራ ፋኖ በይፋት ከ3 ወራት በላይ የሰለጠኑ አባላቱን አርማኒያ ላይ  በድምቀት አስመርቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ የአማ…

የአማራ ፋኖ በይፋት ከ3 ወራት በላይ የሰለጠኑ አባላቱን አርማኒያ ላይ በድምቀት አስመርቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማ…

የአማራ ፋኖ በይፋት ከ3 ወራት በላይ የሰለጠኑ አባላቱን አርማኒያ ላይ በድምቀት አስመርቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ በይፋት በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ በአርማኒያ እና በማፈፉድ ቀበሌ ከ3 ወራት በላይ ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በድምቀት አስመርቋል። የአማራ ፋኖ በይፋት አርማኒያ ላይ በርካታ ፋኖዎችን ግንቦት 1/2014 በደማቅ ስነ ስርዓት አስመርቋል። በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይም የፋኖ አስተባባሪ፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ አሰግድ መኮንንን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝቷል። ከምኒልክ ፋኖ በሸዋ ፋኖ አብዮት ወርቁን ጨምሮ ከአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከተማ እና ከማጀቴ ከተማ እንዲሁም ከይፋትና ከማፉድ ቀበሌ የመጡ የፋኖ አባላት ባሉበት ምርቃቱ ተካሂዷል። ተመራቂ የአርማኒያ እና የማፉድ ፋኖ አባላትም ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን አሳይተዋል፤ የስነ ጽሁፍ ስራቸውንም አቅርበዋል። ድምጻዊ አሸብር በላይ፣ ድምጻዊ እና ገጣሚ ያብባል ደሴ እና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች በመድረኩ ተገኝተው ደማቅ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል። እንዳለው ዘውዱ እና የምሩ በለጠው የተባሉ ሁለት ተማሪዎች ከወዳደቀ ብረታ ብረት የሰሩትን መሳሪያ የመትረጊስ ጥይት በመተኮስ የሚሰራ ስለመሆኑ በሙከራ አረጋግጠዋል፤ ከበዓሉ ታዳሚዎች ከፍተኛ አድናቆትን አትርፈዋል፤ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ተጠይቋል። በመድረኩም ለተመራቂዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶችን ጨምሮ ፋኖን የሚያጠናክሩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ተከናውኗል። ለፋኖ አሰልጣኞችና አመራሮችም የሽልማት እና የእውቅና ሽልማት ስነ ስርዓትም ተካሂዷል። የሀይማኖት አባቶች መድረኩን በጸሎት እንደከፈቱት ሁሉ በምርቃት እና ፋኖዎች ለወገናቸው መከታ እንዲሆኑ ቃል አስገብተዋል። በመጨረሻም የሸዋሮቢት ፋኖ መሪ ፋኖ መከታው ማሞ ለመድረኩ አዘጋጆችና ለተሳታፊዎች ሁሉ ምስጋና በማቅረብ መድረኩ ፍጻሜውን አግኝቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አርማኒያ ላይ ተገኝቶ ሙሉ የምርቃት ስነ ስርዓቱን ተከታትሏል። ሙሉ ዝግጅቱን በዩቱብ አድራሻችን ይለቀቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply