
የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት የምስራቅ አማራ ፋኖ ሃውጃኖ ብርጌድ ራያ አላማጣ ዋጃ ጥሙጋ ከተማ ላይ ለሶስት ወር ያሰለጠናቸዉን ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት የምስራቅ አማራ ፋኖ ሃውጃኖ ብርጌድ ራያ አላማጣ ዋጃ ጥሙጋ ከተማ ላይ ለሶስት ወር ያሰለጠናቸዉን ፋኖዎች በደማቅ ሁኔታ ማስመረቁን አስታውቋል፡፡ ከጀግኖቹ ከነ ይርጋ አበበ (ሃውጃኖ) ከነ ፋኖ ሞላ ደስየ የትውልድ ቦታ ራያ አላማጣ እና አካባቢው የተጀመረው ፋኖን የማሰልጠን እና የማደራጀት ስራ በቀጣይም ወደ ሌሎች የራያ አካባቢዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ “የተደራጀ ህልዉናው የተረጋገጠ አማራ ለኢትዮጵያ አንድነት!” “ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው፡፡” ራያ አላማጣ ወሎ አማራ ኢትዮጵያ!
Source: Link to the Post