የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ወደ አንድ መምጣቱን እውቅና ለመስጠትና ለማብሰር በሚል ያዘጋጀው መድረክ በመካሄድ ላይ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም…

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ወደ አንድ መምጣቱን እውቅና ለመስጠትና ለማብሰር በሚል ያዘጋጀው መድረክ በመካሄድ ላይ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ከተማ ማራኪ አካባቢ በኪዊንስ ሆቴል አዳራሽ መጋቢት 11/2014 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በጎንደር እና አካባቢው በተለያዩ የብርጌድ እና የሻለቃ አደረጃጀቶች የታቀፉ የአማራ ፋኖዎች ወደ አንድ ማዕቀፍ መምጣታቸውን ለማሳወቅ ያለመ ታላቅ መድረክ ነው። በመድረኩም በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ስለሀገር እና ስለወገን ሲሉ ከፍተኛ ዋጋ የከፈሉ በርካታ ሀገር ወዳድ አርበኞች፣ ምሁራንና ወጣቶች እየተሳተፉበት ነው። እንዲሁም የሚዲያ ተቋማትን የወከሉ ጋዜጠኞች፣የኪነ ጥበብ ሰዎች እና ሌሎች የክብር እንግዶች የታደሙበት ልዩ መድረክ ነው። ይህ አደረጃጀት በቀጣይ በልዩ ልዩ ምክንያቶች በማዕቀፉ ውስጥ ያልታቀፉ በጎንደር የፋኖ አባላትን ሁሉ በማካተት እንዲሁም በጎጃም፣ በወሎ፣ በሸዋ እና በሌሎች አካባቢዎች ካሉ መዋቅሮች ጋር የበለጠ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመስራት ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። መጋቢት 11/2014 ራሱን ያስተዋወቀው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ጭምር ለመታደግ የሚያስችል እንደሚሆን በመግለጫው ተካቷል። የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አንድነቱን በሚያስተዋውቅበት ልዩ የአብሮነት መድረኩ ላይ የፋኖን ታሪካዊ የተጋድሎ ዳራ፣አላማ፣ግብን፣ላመኑት ነገር መስዋዕትነት መክፈልን፣ ህጋዊነትን፣አቃፊነትንና ህዝባዊ ወገንተኝነት ሁሉ አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን አሚማ ለመገንዘብ ችሏል። የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢዎችም ይፋ እንደሚደረጉ ይጠበቃል። በጎንደር ከተማ የተገኘው አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተጨማሪ መረጃዎችን ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply