You are currently viewing የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት አካልን ነጻ የማውጣት ክስ መሰረቱ፤ ለጳጉሜ 3 ቀን በባሕርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጳጉሜ 1 ቀን…

የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት አካልን ነጻ የማውጣት ክስ መሰረቱ፤ ለጳጉሜ 3 ቀን በባሕርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 1 ቀን…

የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት አካልን ነጻ የማውጣት ክስ መሰረቱ፤ ለጳጉሜ 3 ቀን በባሕርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ፋኖ አንድነትን ለማመቻቸት በባህርዳር ስብሰባ ላይ በነበሩበት ወቅት በመንግስት የፀጥታ ኃይላት በድንገት ታፍሰው በባህርዳር ሳባታሚት ማረሚያ እየተሰቃዩ የሚገኙ የፋኖ አባላት በአካል ነፃ የመውጣት አቤቱታ አቅርቧል። ከተያዙበት ዕለት ጀምሮ በባህርዳር ጠቅላይ ፍ/ቤትጉዳያቸው ታይቶ ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም ለእያንዳንዳቸው 25 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑ ይታወሳል። በውሳኔው መሰረት የዋስትና ገንዘቡም ተከፍሏል። ይሁን እንጅ በኦህዴድ ብልፅግና አዛዥነት እና በብአዴን ይሁንታ የፍ/ቤት ትዕዛዝ በመጣስ ላለፉት 40 ቀናት ታግተው ይገኛሉ። ይህን ተከትሎ የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላት በአካል ነፃ የመውጣት አቤቱታ ለባህርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበዋል። አቤቱታውን ተከትሎ ፍ/ቤቱ ጉዳዮን ለመመልከት ለጳጉሜ 3/2014 ዓ.ም ቀጥሮታል። ስለሆነም በባህርዳር እና አካባቢዋ የምትገኙ አካላት በሙሉ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በከፍተኛ ፍ/ቤት በመገኘት ችሎቱን እንድትከታተሉ እና ደጋፋችሁን እንድታሳዩ ፋኖዎች ጥሪ አቅርበዋል ሲል ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply