የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዝክረ ሰማዕታት እና የተሃድሶ ፕሮግራም በስኬት ተጠናቀቀ! ታሕሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አ…

የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዝክረ ሰማዕታት እና የተሃድሶ ፕሮግራም በስኬት ተጠናቀቀ! ታሕሳስ 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዝክረ ሰማዕታት እና የተሃድሶ ፕሮግራም በራያ ቆቦ ወረዳ 042 ቀበሌ ልዩ ስሟ ጎለሻ በምትባል ቦታ በደማቅ ሁኔታ ታስቦ ውሏል። በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ፋኖ አንድነት ዋና አዛዥ ሻለቃ ሰፈር መለሰ የተገኙ ሲሆን የመንግሥት ስልጣንን ሽፋን በማድረግ ፋኖን የማሳነስ እና የማንኳስ ስራ ላይ መጠመዳቸው እንዳሳዘናቸው የገለፁ ሲሆን ፋኖ አገርን ከውርደት የታደገ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑንም ተናግረዋል ። የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ ኃላፊና እና የምስራቅ አማራ ፋኖ ዋና አዛዥ ዋርካው ሻለቃ ምሬ ወዳጆ በበኩላቸው የምስራቅ አማራ ፋኖ ከመከላከያ ጋር በመሠለፍ ብዙ ጓዶች ቢሰውም ታሪክ የማይረሳው ጀብዶ መሥራታቸውን ተናግረዋል። ስለሆነም ያለመስዋዕትነት አሸናፊነት እና ክብር ስለማይገኝ የአገርን ህልውና ለመጠበቅ ሁሉም ፋኖ መሆን አለበት ብለዋል። በዕለቱ በክብር ሰማዕትነትን ለተቀበሉ ፋኖዎች እውቅናና የትግል ታሪካቸው ተነግሯል። የሽልማት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምስል ያለበት ስጦታም ተበርክቷል። አሻራ ሚዲያ በቦታው የተገኘ ሲሆን ሙሉ ፕሮግራሙን በዩትዩብ ቻናላችን የምናቀርብ ይሆናል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply