የአማሮ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች አሁንም የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገለጹ፡፡በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች አሁንም የደህንነት ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ የልዩ ወረዳው የመንግስት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/NXAZ5O1fuijqlw2uFApFY4CWhVDXZClI8U_LUegMoED2EJM5XpqshX5KO4QmO1QiGSq8y-nWHZrmjHr2lD_XGQ26vPd8v2R6rPJpNCVpoYwaOYOpqKHQG0LIKgnytbXGCihwRkasYYevisoyDzrG31GfuF-zj3zH4vsESctwsd1ZE7BVk-8tlIkpOU_gB7AHtf0oEjEO5gagrAQjB4pydk2bDzlYVNhli0HMbuTxTvs11OmEDNFsuqSH9ptftQDxSvRRMxs5qhaQrielnfldPtWi_76w4qJovCxtM4VY7jKyOdIeb5bk2SgtQ1XbrmzR7sK2e0G99vAjdECAGDm41A.jpg

የአማሮ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች አሁንም የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገለጹ፡፡

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች አሁንም የደህንነት ስጋት ውስጥ እንደሚገኙ የልዩ ወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡
የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ፍጹም አራጋው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣በልዩ ወረዳው የሚጀመሩ የኦፕሬሽን ስራዎች ስለሚቋረጡ ነዋሪው ሙሉ በሙሉ ከስጋት አልወጣም ብለዋል፡፡

አሁን ላይ አንጻራዊ ሰላም እንዳለ የተናገሩት ሃላፊው፣ በአንዳንድ ቦታዎች አርሶ-አደሮች የበልግ እርሻ መጀመራቸውን አንስተዋል፡፡
ነገር ግን ልዩ ወረዳውን ከሚያዋስኑ ቀበሌዎች መካከል አንዱ ከሆነው ገላና ቀበሌ ሸኔ ጨርሶ እንዳልወጣ ገልጸዋል፡፡

አክለውም በታዛኒያ ይደረጋል በተባለው የድርድር ዋዜማ የሽብር ሃይሉ ሁለት የቀበሌ አመራሮችን ገድሏል ነው ያሉት፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት እና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ሃይል መካከል የሚደረገው ድርድር ለወረዳው ሰላም ትልቅ አስተዋእጾ እንዳለው አቶ ፍጹም ተናግረዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply