የአማዞን ቀጣይ ስራ አስፈጻሚ ይሆናል የተባለው ኤንዲ ጄሲ ማነው?

አዲስ አበባ፣ጥር 27፣ 2013 የአማዞን ቀጣይ ስራ አስፈጻሚ ይሆናል የተባለው ኤንዲ ጄሲ ማነው? ከዓለማችን ቁንጮ ቱጃሮች መካከል 2ኛው የሆነው ቤዞስ በግዙፉ የዓለማችን የበይነ መረብ ግብይት ተቋም አማዞን ያለውን ኃላፊነት ለሌላ ሰው እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡ ቤዞስ የአማዞን መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ነው፡፡
ትኩረቱን ወደ ሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች የማዞር ውጥን እንዳለው ያስታወቀው ቤዞስ ዋና ስራ አስፈጻሚነቱን በመጪው ክረምት ለተቋሙ የ‘ክላውድ ኮምፒውቲንግ’ ስራ ክፍል ኃላፊ ኤንዲ ጄሲ እንደሚያስረክብ ነው ያስታወቀው፡፡ የኒውዮርክ ተወላጁ እና የሃርቫርድ ተመራቂው የቢዝነስ ሰው ጄሲ ያኔ አማዞን እየታወቀ መምጣት በጀመረበት እ.ኤ.አ በ1997 ነበር በጀማሪ ሰራተኛሪነት ድርጅቱን የተቀላቀለው፡፡
ግብይትን ጨምሮ በተለያዩ የአመራርነት እርከኖች ያገለገለ ሲሆን በፈረንጆቹ ሚሊኒዬም መባቻ ግድም በነበሩት ዓመታት ከሌሎች 57 ባልደረቦቹ ጋር በመሆን የአማዞንን የድረገጽ ግብይት አገልግሎት አስጀምሯል፡፡ የአገልግሎቱ ምክትል ሃላፊ ከዚያም ዋና ኃላፊ በመሆንም ሰርቷል፡፡ ድርጅቱ የመረጃ ቋትን መሰረት ባደረጉ አገልግሎቶች(‘ክላውድ ኮምፒውቲንግ’) ልቆ እንዲወጣ ካስቻሉ የድርጅቱ አመራሮች መካከል አንዱ መሆኑ ይነገራል፡፡(AL AIN)

Source: Link to the Post

Leave a Reply