የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Brlj_eHigzEIWGDHv-iL0__3hkeOfjq1YyHnUKLnB-WAG3ljhnA6ncPBilCd7Lsf4_MLC0-Mr-aAJF2UwxWvByHuWBas7Bsl4r47isEkQdBPjqHm2kz29AyUc11ml4BC0-KFwNfvx04rej-8S5LIYd7y7j5Gt5DzmLgZbYx3mx877m7ko5HWxYRwczt3BM9zEIdxypGdTj1dtXlN0n6w3nkMBgoccq3N7zcq7sCdvMoDv9PN2TSmuAyyit5YxGgmeWtonwLl9Vp6SUetwZQnR_ArPTkB6Suh9LoqVnFaMWiuFR_xmyIggN_5ii_6fZwqaip4HevOftDPSi_KXS8TVQ.jpg

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ፣ አምባሳደር ኢንጅነር ሥለሺ በቀለ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በኢትዮጵያ በሚያደርጉት የስራ ጉብኝት በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች፣ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የነበረው ግጭት ስለተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸምና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቆይታቸው ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሐማት ጋር በዓለም አቀፋዊና ቀጠናዊና መሰል ጉዳዮች ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።

ከሲቪል ማኅበረሰብ አባላትና ከሰብአዊ እርዳታ አጋሮች በመገናኘት በምግብ ዋስትና፣ በእርዳታ አቅርቦትና በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩም የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply