የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሆስፒታል በመግባታቸው የኔቶ ስብሰባቸውን ሰረዙየአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በወራት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ሆስፒታል በመግባታቸው ለሰሜን አትላንቲክ የጦ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/BMiGTdBDxB3omR1x0VUulcPh5eqXtvZbiaJsg-HceRaU8kAxIEPcDXYyCuu67hHZtRjNDLZJ7iiWiXmkwQTeyNAW247Cx4qaNazSIDD5AbkTdu-PwTI3nzqZce_XyfCjH4eeru8MF7vi4KBMTWweH57_x-nXHIUgv3bOaEmVdzltrwIrgFHfTBk5BhJgODs_LNTLycoJG72QLERtiYz6fdI6sqqNOBpD2qAnNtWs5FIUdPaAJ3EqTh368tq-Tc3fv-6drJgfxEA6EZY3YfKWb2ZgAJKRGfHeQRpSTqT8A-TaCvatVbCaKi5ChVxKh205SMQ-UzUBVEqo2TgiDAC2qg.jpg

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሆስፒታል በመግባታቸው የኔቶ ስብሰባቸውን ሰረዙ

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን በወራት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ሆስፒታል በመግባታቸው ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ስብሰባ የሚያደርጉትን ጉዞ ሰረዙ።

የ70 ዓመቱ ኦስቲን ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ ሆስፒታል ጥብቅ የሕክምና ክትትል በሚያስፈልጋቸው ህሙማን ክፍል ውስጥ ናቸው።

ፔንታገን እንዳለው ሚኒስትሩ ሆስፒታል የገቡት ድንገተኛ የሽንት ፊኛ ችግር ገጥሟቸው ነው።

ኦስቲን ማክሰኞ ወደ ሥራቸው እንደሚመለሱ ተስፋ እንዳለው ፔንታገን የገለጸ ሲሆን ለጊዜው ግን ያለባቸው ኃላፊነት ለምክትላቸው ተላልፏል ብሏል።

ሰኞ ዕለት በፔንታገን የወጣው የዋልተር ሪድ የጦር ሆስፒታል ባለሥልጣናት መግለጫ እንዳለው ሚኒስትሩ ለተራዘመ ጊዜ ሆስፒታል ውስጥ ይቆያሉ ተብሎ አይጠበቅም።

ሆኖም የመጀመሪያ ጥቁር የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሆስፒታል ውስጥ የሚቆዩት ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ አልተጠቀሰም ።

አሁን ላይ ኦስቲን ያጋጠማቸው የሽንት ፊኛ ችግር ከካንሰር እንደሚያገግሙ የተጣለውን ተስፋ እንደማይለውጥም ተነግሯል።

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply