የአሜሪካ መከላከያ ጦር ሀላፊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ሊያስገቡ ነው ተባለ፡፡አሜሪካ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶችን በመጠባበቅ ላይ ሳለች የሀገርቱ መከላከያ ሚኒስትር ማርክ እስፔር የስልጣን መ…

የአሜሪካ መከላከያ ጦር ሀላፊ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ሊያስገቡ ነው ተባለ፡፡

አሜሪካ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቶችን በመጠባበቅ ላይ ሳለች የሀገርቱ መከላከያ ሚኒስትር ማርክ እስፔር የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ሊያስገቡ አዘጋጅተዋል ሲል NBC ኒውስ በዘገባው አመላክቷል፡፡

የአሜሪካው ዜና አውታር 3 አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙ የመከላከያ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ እስፔር ደብዳቤውን ያዘጋጀው ከምርጫው በኋላ ይገፋሉ ተብሎ ከሚጠበቁት ባለሥልጣናት አንዱ ስለሆነ ነው ማለታቸውን ገልጿል፡፡

ትራምፕ በዚህ የበጋ ወቅት የተቃውሞ ሰልፎችን ለማብረድ ብሔራዊ ጥበቃን በመጠቀማቸው ከመከላከያ ሀላፊው ጋር ለረጅም ጊዜ ሲጣላ መቆየታቸውን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

እስፔር የኮንፌዴሬሽን አመራሮች ስም ከወታደራዊ ካምፖች እንዲወጡ የሚያስችል ረቂቅ ሕግ ላይ የኮንግሬስ አባላትን እየረዳ እንደሚገኝም ነው የተገለፀው፡፡

በሁሉአገር አተሮ
ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply