የአሜሪካ ኤምባሲ “ቴክ ካምፕ አዲስ” የተሰኘ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ፕሮጀክት አስጀመረ

ሰኞ መስከረም 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ “ቴክ ካምፕ አዲስ” የተሰኘ የአንድ ዓመት የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ፕሮጀክት አስጀመረ፡፡

ኤምባሲው ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ከአሜሪካ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በ “ቴክ ካምፕ አዲስ” ፕሮጀክት ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ 60 ሰዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ በመጀመሪያ ወርክሾፕ የተሳተፉ ሰዎች ያገኙትን ልምድና ክህሎት የወርክሾፕና ስልጠና ዕድሎችን ለማኅበረሰቡ በማመቻቸት በሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ላይ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ ይሰራሉ ተብሏል፡፡

“ቴክ ካምፕ አዲስ” የሚዲያ ክህሎትን እና ኃላፊነት የተሞላበት ዘገባ ማቅረብን ለማጠናከር፣ እንዲሁም የወርክሾፖች እና የስልጠና ዕድሎች በማመቻቸወት ሙያዊ ጋዜጠኝነትን ለማጠናከር የተነደፈ ነው መሆኑን ኤምባሲው ጠቁሟል።

The post የአሜሪካ ኤምባሲ “ቴክ ካምፕ አዲስ” የተሰኘ የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎት ፕሮጀክት አስጀመረ first appeared on Addis Maleda.

Source: Link to the Post

Leave a Reply