የአሜሪካ ኤርፖርቶች በመንገደኞች ተጨናንቀዋል፡፡ በሃገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ኤርፖርቶች መንገደኞችን በማስተናገድ መጠመዳቸውን ነው አልጀዚራ ያስነበበው፡፡ ባሳለፍነው እሁድ የአሜሪካ ኤርፖርቶች በ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/eObJxcURF7PC23ntcxn_z00CSqLB3TJnRDroIHgta8yXj_RUdyvQ635tGDoD_hPn5zm6ZhNa8Bjdl6iNSl0dzcyoUU9HV3czgouxlqQfpA_bL5MkkEdnA2OB-LZkgvmPVgTjdWLFyfJrvYFnDxqx6gvaCvszHtbkNEUSG5Ha-mFUjIrCkTZB_y8HyimGQz4dJ8hSeyhVESKoH8zQlIXjYq3DOltfo78lV5jb5fW7NaIaOAUgOFBLKixmrOVCCwRQqKnIr4h5qsWjyY-nBdTIcUH2dNOBUBy6oU3VHqYtjrx-TKI2z-8uggmwLtm03groh9W16MV7JeADkv---8zHAg.jpg

የአሜሪካ ኤርፖርቶች በመንገደኞች ተጨናንቀዋል፡፡

በሃገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ኤርፖርቶች መንገደኞችን በማስተናገድ መጠመዳቸውን ነው አልጀዚራ ያስነበበው፡፡

ባሳለፍነው እሁድ የአሜሪካ ኤርፖርቶች በርካታ መንገደኞች ያስመዘገቡበት ታሪካዊ ቀን ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
የአሜሪካ የትራንስፖርትና ደህንነት አስተዳደር እንዳለው ከሆነ ከኮሮና ቫይረስ ማብቃት በኃላ ኤርፖርቶቻችን በታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መንገደኛ አስተናግደዋል ብሏል፡፡

በዚህም በአንድ ቀን ብቻ የሃገሪቱ ኤርፖርቶች ሶስት ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዳቸውን ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው፡፡
ኤርፖርቶቹ በየ አንድ ሰከንድ ውስጥ 35 መንገደኞች ተቀብለው ማስተናገዳቸውን ነው መረጃዎች የጠቆሙት፡፡
የአሜሪካ አየር መንገዶች በቀጣዮቹ የክረምት ወራት በቀን 26 ሺህ በረራዎችን ለማድረግ እቅድ እንዳስቀመጡም ተገልጿል፡፡

አሜሪካ ባሳለፍነው ዓመት ክረምት ወራት ውስጥ 255 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናገዱ ሲሆን የዘንድሮው መንገደኞች ቁጥር በ10 በመቶ እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply