የአሜሪካ እና የሩስያ መሪዎች ጠብ አጫሪ ቃላትን መሰነዛዘር ጀምረዋል::ትናንት ማምሻውን በርካታ ሰዎች በሚገኙበት መካከል የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የሩስያውን ፕሬዝደንት ፑቲንን የጦር…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/i5IlN6BImkYfGYzc06HHhCmLEXUD-z3WK9VPt35FRkBWU_bToVoyzg5_CqGUjx9_Vu0lHNV21Eoh8aS9UpxgJ7Hb6FMsHDDcY7g-I2SBGaW7Iii7f3sxvvy1jgykzDqXwQLI3i9A6b3VMv8zGqxdcKS_uMA8pfg9HkuBxeJhXHePm0Tn27asNzft7RIzTcyY4QllT0V91NlAPnEjGkxljYFEaVyT9ETkUowUkvEk26syJxMNoaATz1o6hdB3RsyR24VbOcRZ-ItoeJ08Npevh7Vi8PK9sPRolOaNkV3smIemfkTZb9xyfkg3zgWDPRWvxnkNkG3ue8iHSAjHojCl5g.jpg

የአሜሪካ እና የሩስያ መሪዎች ጠብ አጫሪ ቃላትን መሰነዛዘር ጀምረዋል::

ትናንት ማምሻውን በርካታ ሰዎች በሚገኙበት መካከል የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባይደን የሩስያውን ፕሬዝደንት ፑቲንን የጦር ወንጀለኛ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባይደን ስለ ፑቲን ከሰዎች ለተነሳላቸው ጥያቄ የጦር ወንጀለኛ ነው ሲሉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ የትስስር ገፆች በሰፊው ተሰራጭቷል፡፡
ለሊቱን ለፕሬዝደንት ባይደን ንግግር የሞስኮው ክሬምሊን ቤተ-መንግስት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ክሬምሊን በፑቲን ላይ የተሰነዘረውን ውንጀላ ተቀባይነት የሌለው እና ምህረት የማይገባው ሲል አጣጥሎታል፡፡

የምእራባዊያን መሪዎች በተደጋጋሚ የሩስያውን ፕሬዝደንት ስም እየጠሩ ማጣጣላቸውን የቀጠሉ ቢሆንም፣ ከሩስያ በኩል የሚሰጠው ምላሽ ለዘብተኛ ሆነው የሚታወቁ ቢሆንም በአሁኑ የባይደን ንግግር ግን ዝምታን አልተመረጠም፡፡

የክኦኤምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንዲህ ያለ ንግግር በመላው አለም መቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በቦንብ ከፈጀች ሃገር መሪ የማይጠበቅ ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

አር-ቲ

አብድልሰላም አንሳር
መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply