
የአሜሪካ ኮንግረስ አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ለማረፍ መቃረባቸውን ተከትሎ ቻይና አካባቢውን ለሲቪል በረራዎች ዝግ አድርጋለች፡፡
የናንሲ ወደ ታይዋን ማምራት በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት ያነገሰ ሲሆን ታይዋንም የህግ ስርአቷን ጠበቅ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡
ናንሲ ፔሎሲ የሚገኙበት አውሮፕላን በታይዋን የጦር ጀቶች ከመታጀባቸው ባሻገር፣ የአሜሪካ 4 የባህር ሃይል መርከቦች ማምራታቸውን የአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን አስታውቋል፡፡
የቻይና የጦር ጀቶች በተደጋጋሚ የታይዋንን የአየር ክልል ሲጥሱ መዋላቸውን ሪፖርቶች አመላክተዋል፡፡
በአብዱሰላም አንሳር
ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ
ይሁኑ ።
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast
ዌብሳይት https://ethiofm107.com/
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።
Source: Link to the Post