የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን 61 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ አዋጅ አፀደቀ

የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከወራት ክርክር በኋላ ለዩክሬን በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች ወታደራዊ እርዳታ ለማድረግ ውሳኔ አሳልፏል።

በኮንግረሱ ብዙ ተቃውሞ ገጥሞት የነበረው ይህ የ61 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ዩክሬን ራሷን ከሩሲያ ወረራ ለመመከት ያግዛታል ተብሏል።

አሁን ድጋፉ ‘መቼ’ ነው ለዩክሬን የሚደርሰው የሚለው ጥያቄ መነጋገሪያ ሆኗል። ምናልባትም በቀናት ውስጥ እርዳታው ለዩክሬን መድረስ እንደሚጀምር መላ ምቶች አሉ።

የሩሲያ ጥቃትን ለመከላከል እጅግ ወሳኝ ለሆነው ወታደራዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን የገለጡት የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ፤ “ዴሞክራሲ እና ነፃነት ሁሌም ዓለም አቀፍ ጠቀሜታ አላቸው፤ አሜሪካ ድጋፍ ማድረግ ከቀጠለች ደግሞ መቼም ቢሆን አይከስምም” ብለዋል።

አክለው ድጋፉ ጦርነቱ እንዳይስፋፋ ከማድረጉም በላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ይታደጋል ብለዋል።

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ በበኩላቸው እርዳታው “አሜሪካን የበለጠ ሀብታም ያደርጋታል፤ ዩክሬንን ደግሞ የበለጠ ያላሽቃታል አልፎም ለበርካታ ዩክሬናዊያን ሞት ምክንያት ይሆናል” ብለዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply