የአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት በሀገሪቱ የቲክ ቶክ ማህበራዊ ሚዲያን የሚያግደውን ረቂቅ ህግ አወጣ።

435 መቀመጫ ያለው ምክር ቤቱ በ352 የአብላጫ ድምፅ ቲክቶክን በአሜሪካ ምድር እንዲታገድ የሚጠይቀውን ህግ እንዲፀድቅ ውሳኔ አሳልፏል።

ህጉ ለላይኛው ምክር ቤት ቀርቦ ተቀባይነትን የሚያገኝ ከሆነ ወደ 170 ሚሊየን አሜሪካውያን የሚጠቀሙት የቲክቶክ መተግበሪያን የማገድ ውሳኔው ይፀድቃል ተብሏል።

ባይትዳንስ በተሰኘው የቻይናው ኩባንያ የሚተዳደረው ቲክቶክ በአሜሪካ እግድ እንዳይጣልበት ባለቤትነቱን ለአሜሪካ እንዲሸጥ ጥያቄም ቀርቦለታል ተብሏል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፤ ቲክቶክን ለማገድ በሚቀርብላቸው ውሳኔ ላይ ፊርማቸውን ለማኖር ፍቃደኛ መሆናቸውን ባሳለፍነው ሳምንት ማሳወቃቸው ይታወሳል።

በሐመረ ፍሬው

መጋቢት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply