የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ከክረምት በፊት ከስልጣናቸው እንደሚለቁ ተነገረ

ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁ ምንጮች  ሰማሁት ብሎ ሮይተርስ እንደዘገበው  ምክትላቸው ፔይቶን ኖፕፍ ቦታውን እንደሚረከቡ ይጠበቃል ብሏል።

ፌልትማንን የተኩት  ሳተርፊልድ  አስከአሁን በቦታው ላይ  ስድስት ወር የሰሩ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ስራውን ይለቃሉ ተብሎ ግን  አልተጠበቀም ነበር ።

በቦታው ላይ  ቶሎ ቶሎ ሀላፊዎች መቀያየር የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ ላይ የባይደን አስተዳደር   እንደተፈተነ ያሳያል ሲሉ ፖለቲካ ተንተኞች ይገልፃሉ።

ሳተርፊልድ   የፊታችን ረቡዕ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናትንም ያነጋግራሉ ተብሎም ሲጠበቅ ነበር ።

The post የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ሳተርፊልድ ከክረምት በፊት ከስልጣናቸው እንደሚለቁ ተነገረ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply