የአሜሪካ የዲሞክራሲ ሚስጢር ያለዉ ተቋማቱ ላይ ነዉ፡- ————- ሸንቁጥ አየለ  ———–'  ምርጫ ቦርድ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት የእዉቅና ሰርተፍኬት ሊሰጠዉ አይገባም የሚ…

የአሜሪካ የዲሞክራሲ ሚስጢር ያለዉ ተቋማቱ ላይ ነዉ፡- ————- ሸንቁጥ አየለ ———–' ምርጫ ቦርድ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት የእዉቅና ሰርተፍኬት ሊሰጠዉ አይገባም የሚ…

የአሜሪካ የዲሞክራሲ ሚስጢር ያለዉ ተቋማቱ ላይ ነዉ፡- ————- ሸንቁጥ አየለ ———–‘ ምርጫ ቦርድ ለተመራጩ ፕሬዝዳንት የእዉቅና ሰርተፍኬት ሊሰጠዉ አይገባም የሚለዉ የትረም ደጋፊዎች ተቃዉሞ በቫይስ ፕሬዝዳንት ፔንስ ሊቀመንበ…ርነት በግሩም ክርክር እየተከናወነ ነዉ። ሀሳቡን የሚደፍም የሚቃወምም በታላቅ ሀገራዊ ስሜት ሀሳቡን ያስረዳል። ከሁሉም መሳጭ ንግግር የሚያደርጉት ደግሞ ከሪፐብሊካን ወገን የሆኑት እና ትረምፕ ዲሞክራቲክ ሀገራዊ እሴቱን እየገደለ ነዉ ብለዉ የሚከራከሩት ነዉ። የነሱ ጥብቅና ለሪፐብሊካን ፓርቲያቸዉ ሳይሆን ለአሜሪካ ነዉ። ንግግራቸዉ ያስደምማል። ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሪፐብሊካን ተወካዮች የባይደንን ፕሬዝዳንትነት መቀበል አለብን ብለዉ በገሃድ የሚከራከሩ እና ድምጻቸዉንም ለዚሁ ሂደት የሰጡ ናቸዉ። ሀገር ከፓርቲም፡ ከግለሰቦችም በላይ ነዉ የሚል አቋም በማራመድ ከዲሞክራቶች ጋር ቆመዋል። እግዚአብሄር እንዲጸና ሲፈቅድ የተዋጣላቸዉ ተቋማት መሰረት እንዲኖራቸዉ ያደርጋል። ትረምፕን የሚያመልኩ ስሜታዊ ሪፐብሊካን ቢኖሩም፡ ቁጡ ደጋፊዎች ቢኖሩም ፡ ዛሬ ቀን የትረም ደጋፊዎች ተቋማቱ ስራቸዉን እንዳያከናዉኑ እንቅፋት ቢፈጥሩባቸዉም አሁን ሌሊቱን ቁጭ ብለዉ የሀገሪቱ ተወካዮች ስራቸዉን ተግባብተዉ እየሰሩ ነዉ።ትረምፕን የመሰለ እጅግ አምባገነን እና ለዲሞክራሲ አልገዛም ባይ ሰዉ ቢያጋጥምም ተቋማቱ ከፕሬዝዳንቱ በላይ መሆናቸዉን በተደጋጋሚ እያሳዩ ነዉ። የየአሜሪካ ዲሞክራሲ በተቋማቱ ጥንካሬ ላይ እንደቆመ የሚያስመሰክር ስራ እየሰሩ ነዉ። የትረም ታማኝ ታዛዥ ነዉ እየተባለ የሚብጠለጠለዉ ፔንስ ታማኝነቴ ለህገመንግስቱ እና ለአሜሪካ ብቻ ነዉ ብሎ ቆምጨጭ ያለ የሀገራዊ አርበኝነት ስራዉን እያከናወነ ነዉ። የአሜሪካኖች አስደማሚ ጉልበት ሚስጥሩ ተቋማት መገንባት መቻላቸዉ ነዉ። አሁን በዚህ ሌሊት ይሄን ሂደት እየተከታተልኩ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ህዝብ በህሊናዬ ይመላለሳል። ኣሁን አሁን ደሞ ብሶብኛ:: ከምጽፈዉ እያንዳዱ ኮድ ዉስጥ ፡ በመስሪያ ቤት ስብሰባ ላይ ፡ በህልሜ ሳይቀር ገጽታ በገጽታ ኢትዮጵያን አነባታለሁ። የሚገናኘዉም የማይገናኘዉም ነገር ላይ ኢትዮጵያ ተጽፋ አነባታለሁ። አሁን የአሜሪካንን ተቋማት እና በተቋማቱ ዉስጥ በመርህ የሚመላለሱትን አምባገነን ግለሰብን ሳይሆን ሀገርን አስቀድመዉ የሚሰሩትን ተወካዮች እያስተዋልኩ ኢትዮጵያን አስባለሁ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እያገላበጥሁ አነባታለሁ። አንዳንዴ ብንን ስል ልቤ በፍርሃት ይርዳል። የማይነበብ ማንበብ የያዝኩ እየመሰለኝ። ቢሆንም ልቤ በኢትዮጵያ ላይ ጽኑ ነዉና እንደገና ኢትዮጵያን ገጽ በገጽ ወደ ማንበብ ገባሁ። አሁንም የአሜሪካንን ተወካዮች እየተከታተልኩ ነዉ። ደህና እደሩ።የኔም ልብ የአሜሪካን ተቋማትን ሚስጢር እያሰስ ኢትዮጵያን ገጽ በገጽ ሲያነብ ያድራል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply