You are currently viewing የአሥራትን ጋዜጠኞች ከሀጫሉ ግድያ በኋላ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል የሚል መዝገብ ተከፈተባቸ

የአሥራትን ጋዜጠኞች ከሀጫሉ ግድያ በኋላ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል የሚል መዝገብ ተከፈተባቸ

ፖሊስ የአሥራትን ጋዜጠኞች ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ንብረት እንዲወድም፣ የሰው ህይወት እንዲጠፋ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለቱ አራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት መዝገብ ተከፍቶባቸዋል።

አራቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ከህዳር 12/2012 ዓ/ም እስከ ሰኔ 12 2012 ዓ/ም ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል መዝገብ ተከፍቶባቸው የነበር ሲሆን በዋስትና ከእስር ሲለቀቁ በሕዳር ወር አሥራትን ከለቀቀው ዮናታን ሙሉጌታ ውጭ ያሉት በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብርና ምስጋናው ከፈለኝ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች ተይዘው ታስረዋል።
በዛሬው ዕለት ፖሊስ በሶስቱ የአሥራት ጋዜጠኞች ላይ ከሀጫሉ ግድያ በኋላ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል መዝገብ ያስከፈተ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 6/2013 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
የመንግስት ባለስልጣናት ከሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ መግለጫ ሲሰጡ አሥራት ሚዲያ ሁከትና ብጥብጥ አስነስቷል በሚል የወነጀሉት ቢሆንም አሥራት ሚዲያ ከሀጫሉ ግድያ ቀድሞ ስራ አቁሞ እንደነበር ይታወሳል።

Leave a Reply