የአራዳ ክ/ከተማ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በገንዘብ የ70 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

የአራዳ ክ/ከተማ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በገንዘብ የ70 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአራዳ ክፍለ ከተማ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በገንዘብ የ70 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡

አመራሮቹና ነዋሪዎቹ “ከሃገራችን አልፎ የአህጉራችን ኩራት፣ አለኝታ እና የድል ተምሳሌት በሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ የተፈጸመውን ክህደት አጥብቀን እናወግዛለን” በሚል መሪ ቃል ነው ድጋፉን ያካሄዱት፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ድጋፉን ይፋ አድርገዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ “ላደረጋችሁት ድጋፍ ሁሉ በራሴ እና በከተማው አስተዳደር ስም ከልቤ አመሰግናለሁ” ብለዋል፡፡

The post የአራዳ ክ/ከተማ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት በአይነትና በገንዘብ የ70 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply