You are currently viewing የአርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት በባ/ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገኝታችሁ አብሮነታችሁን እንድታሳዩ ሲል የአማራ ወጣቶች በባህር ዳር ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር…

የአርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት በባ/ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገኝታችሁ አብሮነታችሁን እንድታሳዩ ሲል የአማራ ወጣቶች በባህር ዳር ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር…

የአርበኛ ዘመነ ካሴን ችሎት በባ/ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ተገኝታችሁ አብሮነታችሁን እንድታሳዩ ሲል የአማራ ወጣቶች በባህር ዳር ጥሪ አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ህዝባዊ ኃይል መሪ አርበኛ ዘመነ ካሴ ነገ ህዳር 12/2015 ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ላይ በባህር ዳር ከተማ እና አካባቢው ከፍተኛ ፍ/ቤት ይቀርባል። የባህር ዳር ከተማ እና የአካባቢው ወጣቶች በስፍራው በመገኘት ችሎቱን እንዲታደሙ የአማራ ወጣቶች በባህር ዳር ጥሪ አቅርቧል። ማህበሩ በአርበኛ ዘመነ ካሴ ችሎት ተገኝተን አጋርነታችን ፣አማራዊ አንድነታችንና ህብረታችንን እንገልፅ ዘንድ የከበረ ጥሪያችን እናስተላልፋለን ብሏል። በተጨማሪም በፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ በአማራ ህዝብ የውሰጥና የውጭ ጠላቶች የታቀደውን አደገኛ ሴራ ከመሪያችንና ከምልክታችን ጎን በመቆም እንድናከሽፍ አማራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ሲል ገልጧል። “የዘመነ መንገድ ፥እጅግ የዘመነ ነው፤ የዘመነ መንገድ የእልፍ አዕላፍ የአማራ ወጣቶች መንገድ ነው፤ መንገዱን በርካቶች ጀምረውታል፤ መንገዱ የሚቋጨው በአማራ ህዝብ ነፃነት ነው።” ብሏል የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር።

Source: Link to the Post

Leave a Reply