You are currently viewing የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምላሽ  ለፍርድ ቤቱ! ለባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት  ጉዳዩ:- የጽሑፍ መልስ ስለመስጠት:- ታሕሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤቱ…

የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምላሽ ለፍርድ ቤቱ! ለባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩ:- የጽሑፍ መልስ ስለመስጠት:- ታሕሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤቱ…

የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምላሽ ለፍርድ ቤቱ! ለባህርዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩ:- የጽሑፍ መልስ ስለመስጠት:- ታሕሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ከፍተኛ ፍ/ቤቱ በቀን 27/03/2015 በቁጥር 0416546 በተጻፈ ደብዳቤ ለህዳር 30ቀን 2015 ዓ.ም ለሆነው ቀጠሮ በአራት ሰዓት እንድቀርብ የማልቀርብ ከሆነም መልሴን በጽሑፍ እንድገልጽ ፍ/ቤቱ ማዘዙ ይታወቃል። በዚህ መሰረት መልሴን በሚከተለው አኳኋን በጽሐፍ አቅርቤያለሁ። “…ክሱ የተመሰረተው ወንጀል ስለሠራሁ አይደለም። ሌላው ቀርቶ እንደደንቡ ለተጠርጣሪነት የሚያበቃ ነጥብ የሚያክል ጉዳይ እንኳን የለም። ክሱ የዐማራ ሕዝብ ጠላቶችና ከዐማራ ሕዝብ ጠላቶች ጋር የተሰለፉ መሰሪ ኃይሎች ፖለቲካ-ወልድ ክስ ነው። በተለይ ላለፉት አራት ዓመታት ንፁህ መሆኔን እያወቁ ስሜን የክስ መዝገብ ላይ ሲጽፉና ሲያደምቁ የሚውሉት ኃይሎች የሚገኙት “ቅረብ” የምባልበት ከፍተኛ ፍ/ቤት ውስጥ አይደለም፤ ቀን ቀን የካድሬ ቢሮዎቻቸው መሸት ሲል በመሰብሰቢያ መጠጥ ቤቶቻቸው ነው። “…የእኔ ከሳሾች እነዚህ በየጊዜው ለዐማራ ህዝብ ውርደት እና አደጋ የሚጎትቱ ኃይሎች እንጂ ዐቃቤ ሕግ አይደለም። ስለዚ ከሄድኩ የምሄደው ወደ እነዚህ ፍልፈል ኃይሎች ቢሮ ወይም ሴራ ሲፈትሉባቸው የሚያነጉባቸው ግሮሰሪዎች እንጂ ፍ/ቤት አይደለም። ክሱ ማታ ግሮሰሪ ውስጥ ይጻፋል ጠዋት የሕግ ቀለም ተቀብቶ ቀድሞኝ ፍ/ቤት ደርሶ ይጠብቃል። በዚህ ዓይነት የዘመኔ የሚያም ቀልድ ውስጥ ለመሳተፍ ተፈጥሮዬ አይፈቅድልኝም። በዕድሜዬ እያወቅሁት ከግፈኞች ጋር ተባብሬ ወይም የግፈኞች መሳሪያ ሆኜ አላውቅም። የግፈኞች ጠላት እንጂ የግፋቸው ድምቀት ሆኜ አላውቅም። መቼም አልሆንም። በዓለም ላይ ብቻየን ብቆም እንኳን ከግፈኞች ጋር ግብግብ መግጠሜን አላቆምም። “…ስለዚህ በግፈኞች እየተጎተትሁ ፍርድ ቤት አልቀርብም። ጠላትን ጀርባውን በመቅደድ እንጂ ጀርባውን በቅቤ በማሸት ለውጥ ይመጣ ይመስል የዐማራን ሕዝብ ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት እልቂት ካወጁ ኃይሎች ጋር ሲተሻሹ የሚውሉት የኛ አሮጌ አሳሞች በትርፍ ጊያቸው እኔ እና መሰሎቼ ላይ የውሸት ክስ ሲጽፉ ይውላሉ። የጠላቶቻችንን ጀርባ ሲያሽ ውሎ በዛለ እጃቸው ወረቀት እና እስክርቢቶ እያገናኙ የፈጠራና የቂም ክስ ሲጽፉ ያመሻሉ። “…የትም የወደቀ ሬሳችን ጅብና አሞራ ግጦት በየስርቻው ስር ወድቆ ያገጠጠ አጥንታችንን ሰብስበው “አዲሲቷ ኢትዮጲያ” የሚሏትን ጠፍ ሀገር “ለመገንባት” ሌት ተቀን ዐማራን የሚፈጁ አውሬዎች ጋር አንሶላ የሚጋፈፉ ጉዶች ጥረው ተጣጥረው ዘመነን እስር ቤት ለማክረም ሲቀዱ ሲሰፉ ይውላሉ። ለማንኛውም ህፃንና ነፍሰጡርን ጨምሮ ዐማራዎች ለቁም በእሳት ሲነዱ ጥቂት እንኳን የማያማቸው እንደ ሰው ከህዋሳት ሳይሆን ከወዳደቀ ብረት የተሰሩ ግኡዝ ኃይሎች የሚጫወቱበት የፍትህ ሥርዓት ውስጥ ፍትሕ ይገኛል ብዬ ፍርድቤት አልመላለስም። ስለዚህ በ30-03-2015 ፍርድቤት አልቀርብም። “…በእኔ ተሞክሮ ከማረሚያ ቤቱ ዋና በር ጀምሮ ዲሽቃና ስናይፐር ተወድሮ፣ በከተማው በሰማይ በራሪ በምድር ተሽከርካሪ ተከልክሎ፣ እንደ እርጥብ ቆዳ ተወጥሮ፣ ወደ ፍርድ ቤት ተወስዶ የሚመለስ ታሳሪ እስካሁን አላውቅም። እኔ ወደ ፍርድ ቤት የምቀርብ ከሆነ ከተማውም ገጠሩም የፊጥኝ ነው የሚታሰረው። ሲቪል ሰርቫንቱ እንኳን ቢሮው ገብቶ ሥራውን መሥራት አይችልም። ጆሮ ጠቢው በየኩይሳው ስር እንደ አሸን ፈልቶ ሰማዩንም መሬቱንም ይሞላዋል። አካባቢው መተንፈሻ ያጣል። ፍርድ ቤት የሚባለው ቦታ የሚሄደው ዘመነ ሳይሆን ግራዚያኒ ነው የሚመስለው። ቤትና ታሪክ ይቁጠራቸው። እና የችሎት ድራማ ላይ (ያውም አላዋቂ ካድሬ የጻፈው ድራማ) ልተውን እየተመላለስሁ ህዝቤን አላስደበድብም። “…የሚገርመው ግሮሰሪ ሞልተው ልብወለድ ክስ የሚጽፉ (የሚደርሱ) ኃይሎች ናቸው ዲሽቃና ስናይፐር እስካፍንጫው የታጠቀ ኃይል እየላኩ “የሚያጅቡኝ” (ሊገሉኝ የሚያደቡኝ)። የሆነው ሆኖ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት ስላለብኝ ፍርድቤት አልቀርብም። ይህ የመጨረሻ የጽሑፍ መልስ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። • (ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም) • (አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ) • ድል ለአማራ ህዝብ ! • ድል ለኢትዮጲያ ህዝብ ! • ዘመነ ካሴ • ከባህርዳር ወህኒ ቤት “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply