የአርበኛ ጎቤ መልኬ መስዋዕትነት 4ኛ ዓመት መታሰቢያ የትግል አጋሮቹ፣ ወጣቶችና ቤተሰቦቹ በተገኙበት በጎንደር ከተማ ተዘከረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም…

የአርበኛ ጎቤ መልኬ መስዋዕትነት 4ኛ ዓመት መታሰቢያ የትግል አጋሮቹ፣ ወጣቶችና ቤተሰቦቹ በተገኙበት በጎንደር ከተማ ተዘከረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም…

የአርበኛ ጎቤ መልኬ መስዋዕትነት 4ኛ ዓመት መታሰቢያ የትግል አጋሮቹ፣ ወጣቶችና ቤተሰቦቹ በተገኙበት በጎንደር ከተማ ተዘከረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አርበኛ ዋዋ ጎቤ መልኬ የተሰዋበትን 4ኛ ዓመት የእረፍት መታሰቢያ ዝክር እና የጧፍ ማብራት ፕሮግራም በዛሬው እለት የካቲት 20 ቀን 2013 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ወጣቶችና በትግል ጓዶቹ አማካኝነት የጎቤ ቤተሰብ በተገኙበት መዘከሩ ተሰምቷል። አርበኛ ጎቤ መልኬ “ሀብት ንብረቴ፣ አይበልጥብኝም ከነጻነቴ” ዱር ቤቴ ያለ ጀግና ሲሆን ህይወቱ በከሃዲ እስክትነጠቅ ድረስ የአማራውን ህዝብ አንድነት ስለማስጠበቅ አብዝቶ ሲሰብክና ሲታገል እንደነበር ይታወቃል። ደፋሩ አርበኛ ጎቤ መልኬ የትግራይ ነጻ አውጭ ነኝ የሚለው የትሕነግ ቡድን በአማራ ላይ እያደርሰ ያለውን ግፍና በደል በማውገዝ ብሎም ወደ ትግል በመሰለፍ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቷል፤ መውጫ መግቢያውን አሳጥቷል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ታጋዩ ዋዋ ጎቤ መልኬ ሀምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጎንደር ከተማ ላይ እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ እነ አታላይ ዛፌ፣ እነ ጌታቸው አደመን እና ሌሎች የኮሚቴ አባላት በወያኔ ሲታፈኑ ጎንደር ከተማ ጦራቸውን ይዘው ከደረሱትና ከታገሉት መካከል አንዱ ነው። እብሪተኛው ትሕነግ አከርካሪ ሊሰብር መጥቶ አከርካሪው በተሰበረበት ቀን በዛች የትሕነግ ቅስም በተሰበረበት ቀን እነ ሲሳይ ታከለ፣ሰጠኝ ባብል እና ሌሎች ጀግኖች መሰዋታቸው ይታወቃል። ትሕነግን መግቢያና መውጫ በማሳጣት በየስፍራው ጦሩ እንዲፍረከረክ በማድረግ ረገድ ጀግናው ጎቤ መልኬና የትግል ጓዶቹ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። በመጨረሻም በቅርቡ እርምጃ በተወሰደበትና በአንድ ቤተሰቡ በኩል በክህደት የካቲት 20 ቀን 2009 ዓ.ም መገደሉ ይታወሳል። በለውጥ እና በአማራዊ ማንነት ትግሉ ተሰልፈው ውድ ህይወታቸውን ከገበሩት አያሌ ጀግኖች መካከል ህዳር 16 ቀን 2009 ዓ.ም ጠገዴ አመራ ቁስቋም ላይ የተሰውት ሙሃቤ በለጠ፣ ሞላአጃው ሙላውና ቃቁ አወቀ ይጠቀሳሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply