የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ከቀዳሚዎቹ የልማትና ዕቅዶች በብዙ መለኪያዎች የተሻለ መሆኑን የፕላንና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ከቀዳሚዎቹ የልማትና ዕቅዶች በብዙ መለኪያዎች የተሻለ መሆኑን የፕላንና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አዘጋጅነት በሚቀርበው ፖሊሲ ማተርስ በተሰኘው መሰናዶ ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት የፕላንና ልማት ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ናቸው ይህንን የተናገሩት፡፡ኮሚሽነሯ በቅርቡ ስለፀደቀው የአስር ዓመት መሪ የብሔራዊ ምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ዕቅድ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዶክተር ፍፁም ይህ መሪ የልማት ዕቅድ ከከዚህ ቀደሞች በተሻለ እንዴት ተግባራዊ ሊደረግ እንደሚችልም አብራርተዋል፡፡ዕቅዱን ከወረቀት ወደ መሬት ለማውረድ አስር ወሳኝ ምሶሶች እንዳሉትም ተናግረዋል፡፡አካታችና ሁሉን አቀፍ ምሶሶች ናቸው ካሏቸው ውስጥም ጥራት፣ የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት፣ ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ኮሚሽነሯ ይህ የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ከቀዳሚዎቹ የሚለይባቸውን ሦስት አንፃሮችም አስረድተዋል፡፡በሦስተኛነት ደግሞ ከዚህ በፊት ባልነበረ መልኩ የህዝብ ተሳትፎ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ይህ የ10 ዓመት የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅዱ እ.አ.አ 2030 ኢትዮጵያን በአፍሪካ ከበለጸጉ አገራት ተርታ ማሰለፍ በልማቱ ሁሉም ዜጋ ፍትሐዊ ተጠቃሚ ለማድረግ ራእይ መሰነቁን አመልክተዋል።

********************************************************

ቀን 27/04/2013

አሀዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply