የአስተዳደር ወሰን፣ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚደረገው ጥናት በግንቦት ወር እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ

የአስተዳደር ወሰን፣ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚደረገው ጥናት በግንቦት ወር እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአስተዳደር ወሰን፣ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚደረገው አጠቃላይ አገራዊ የዳሰሳ ጥናት በመጪው ግንቦት ወር እንደሚጠናቀቅ የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ገለጸ።

በክልሎች መካከል የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸው ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በጥናቱ ይካተታሉ ተብሏል።

ኮሚሽኑ የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ ክንውኑን በተመለከተ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዶክተር ጣሰው ገብሬ እንዳሉት፣ ኮሚሽኑ በአስተዳደር ወሰን፣ በማንነትና ራስን በራስ ማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማቅረብ ለመንግስት ምክረ ሃሳብ ያቀርባል።

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ከ28 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ70 በላይ ተመራማሪዎች የሚሳተፉበት አገራዊ ጥቅል የምርምር ሥራ 40 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።

የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አወል ሁሴን በበኩላቸው ÷ የአስተዳደር ወሰን የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣው ‘አንተም ተው አንተም ተው’ በሚል ሳይሆን በጥናት ላይ በተመሰረተ ውጤት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

The post የአስተዳደር ወሰን፣ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚደረገው ጥናት በግንቦት ወር እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply