የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ተወሰነ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ አካሂዷል።

በስብሰባውም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2015 ባደረገው ስብሰባ የህሕዝብን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ያወጣውን አዋጅ ቁጥር 1299/2015 ለማራዘም የቀረበውን ውሳኔ መርምሮ አፅድቋል።

በዚህም ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 1299/2015 በሁለት ተቃውሞ በሶስት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ለአራት ወራት እንዲራዘም አፅድቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት የሥራ ጊዜ ለማራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ የሥራ ጊዜያቸውን እንዲራዘም አፅድቋል።

ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply