የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከአሁን ቀደም ያስተላለፈው የሰዓት እላፊ ገደብ ለሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት አስታውቋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2014 ዓ…

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከአሁን ቀደም ያስተላለፈው የሰዓት እላፊ ገደብ ለሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት አስታውቋል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በተያያዘ አዲስ መመሪያ አስተላልፏል፡፡ ዕዙ አሁን ባለው አገር የማዳን ግዳጅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን አስታውሷል፡፡ በዚህ ምክንያትም በአንዳንድ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ ገደብ የተደረገ ቢሆንም በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡን ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የምጣኔሃብት ጫና ያሳድራል፤ ኢንዱስትሪዎችንም ያከስራል ብሏል። በመሆኑም የተቀመጠው የሰዓት እላፊ ገደብ ለሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት ነው ያስታወቀው፡፡ ስለሆነም ኢንዱስትሪዎቹ አስፈላጊ የሆነ የራሳቸውን የጥበቃ ስርዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ አጠናክረው መደበኛ ሥራቸውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥሉ እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply