የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ መግለጫየአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻዉን ባደረገው ስብሰባ የዐዋጁን አፈጻጸም ገምግሟል። በግምገማውም አዋጁን በመፈጸም ረገድ የሕዝቡ ተነሣሽነትና ቆራጥነት የ…

https://cdn4.telesco.pe/file/cZC2UslsemXKeV0Ub4kOk0KbDGguiZP_k8G38-l4KXOUwkgRmOQUf7lIyER882B7S0YLtgalWvRtr9IeyYuKbj9QWbJ7UVBFiKpk7WBbkuKYBMY7vNE7zKUDR9EBXEtimpWL8sJPdguwadQvPh4F8X9ig5erxJ0uKS4zaDPxwS1ovZXuCH_PJfvKvQcvoSA5b7NMxnRUMMyjbbZI9OZ5z5VwyxmrY43KoGjAJdgSb0Q7wa9Vxld3H4x1N3E4IMi19v08uaKRyPvbpDQE2kMxQmAQHzj1i6080tr5BScPFnY5edkPtMvTiD9Udp8SlgANFuo01PokqmkpZdDAwf73xg.jpg

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ መግለጫ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ዛሬ ማምሻዉን ባደረገው ስብሰባ የዐዋጁን አፈጻጸም ገምግሟል። በግምገማውም አዋጁን በመፈጸም ረገድ የሕዝቡ ተነሣሽነትና ቆራጥነት የሚደነቅ በመሆኑ ምስጋና አቅርቧል። ያገኘናቸውን ድሎች ጠብቆ ለማስቀጠል እንዲቻልም የሚከተሉትን ትእዛዞች አስተላልፏል።

1. ከአሸባሪው የሕወሐት እጅ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰላምንና ጸጥታን ለማስፈን እንዲሁም የሕዝብንና የንብረትን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ታውጇል።

2. ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች የታወጀውን የሰዓት እላፊ በተመለከተ ወደ አካባቢው የገቡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ፤ እንዲሁም የሰዓት እላፊውን እንዲያስፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷል።

3. ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ መንግሥት ከሚመደብ ሲቪል አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲቋቋም። በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት በአሸባሪው ወራሪ ኃይል በመንግሥት ተቋማት፣ በግለሰብ ንብረቶች፣ በማኅበራዊ ተቋማትና በመሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመትን የሚያሳዩ ማስረጃዎች እንዳይጠፉ እንዲጠበቁ፣ በተገቢው መንገድ እንዲመዘገቡ፣ ማስረጃዎችም እንዲሰነዱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዙ ትእዛዝ ሰጥቷል።

4. የፍትሕ አካላት በየቦታው ከተቋቋሙ ጥምር ኮሚቴዎች ማስረጃዎችን ተቀብለው በማደራጀት ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡ ታዝዟል።

ኅዳር 22 ቀን 2014 ዓም
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ

Source: Link to the Post

Leave a Reply