የአሸባሪውን ህወሓት ኢትዮጵያን የመበተን ሕልም በማክሸፍ ለዜጎቻችን እፎይታ የምንቸርበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ጥቅምት 18/2014 (አሻራ ሚዲያ) የአሸባሪውን ህወሓት ኢትዮጵያን የመበተን ሕልም…

የአሸባሪውን ህወሓት ኢትዮጵያን የመበተን ሕልም በማክሸፍ ለዜጎቻችን እፎይታ የምንቸርበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ጥቅምት 18/2014 (አሻራ ሚዲያ) የአሸባሪውን ህወሓት ኢትዮጵያን የመበተን ሕልም በአጠረ ጊዜ በማክሸፍ ለዜጎቻችን እፎይታ የምንቸርበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ሲሉ ወሎ ግንባር የተገኙ የጎንደር ፋኖ አባላት ተናገሩ። ፋኖዎቹ ኢትዮጵያን ክዶ ሕዝቧን ለስቃይ እየዳረገ ያለውን የአሸባሪውን ቡድን ወራሪ ኃይል አከርካሪ ሰብረን ለመደምሰስ ተዘጋጅተናል ብለዋል። አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል በገባባቸው የወሎ አካባቢዎች በንፁኃን ዜጎች ላይ የጭካኔ ተግባራትን መፈጸሙ እንዳስቆጫቸው ገልጸዋል። ይህን የጭካኔ ተግባርና ወረራ ለማክሰም እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ለመክፈል በቁርጠኝነት እንደሚታገሉም አረጋግጠዋል። ወራሪው አሸባሪ ቡድን ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጥላቻ ሴቶችን በመድፈር፣ ወጣቶችን በመግደል፣ ቤተ እምነቶች፤እንስሳቱን በመግደልእና መሰረተ ልማቶችን በማውደም ዜጎችን ለጉስቁልና መዳረጉንም ተናግረዋል። በመሆኑም የአሸባሪው ቡድን የጥፋት ጉዞ ማክተሚያና የመቀበሪያው ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የወሎና አካባቢዋ ማኅበረሰብ ወራሪውን ኃይል ለማጥፋት በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው ሠራዊት እያደረገ ያለውን የስንቅና ትጥቅ ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል። የፋኖ አባላቱ ደሴ ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። መረጃውን ያደረሠን ኢዜአ ነው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply