You are currently viewing የአሸባሪውን ትሕነግ ወረራ ለመቀልበስ በሚል በአዳርቃይ ማይለሃብ በተደረገው ተጋድሎ በክቡር የተሰውት የእነ ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና አዳነ ጎሹ የተዝካር ስነ ስርዓት የፊታችን ጥር 20 በጎንደር…

የአሸባሪውን ትሕነግ ወረራ ለመቀልበስ በሚል በአዳርቃይ ማይለሃብ በተደረገው ተጋድሎ በክቡር የተሰውት የእነ ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና አዳነ ጎሹ የተዝካር ስነ ስርዓት የፊታችን ጥር 20 በጎንደር…

የአሸባሪውን ትሕነግ ወረራ ለመቀልበስ በሚል በአዳርቃይ ማይለሃብ በተደረገው ተጋድሎ በክቡር የተሰውት የእነ ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና አዳነ ጎሹ የተዝካር ስነ ስርዓት የፊታችን ጥር 20 በጎንደር ከተማ ይካሄዳል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአንድ ቤተሰብ ተገኝተው በአዳርቃይ ማይለሃብ አሸባሪውን ትሕነግ ሲፋለሙ በክብር የተሰውት የእነ ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና አዳነ ጎሹ ተዝካር በጎንደር ከተማ እንደሚከናወን ተገልጧል። ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና ፋኖ አዳነ ጎሹ የተባሉ የወንድማማች ልጆች በሁሉም አማራን ከፈፅሞ ጥቃት የመከላከል ትግል ውስጥ ግንባር ቀደም በመሆን በአማራ ፋኖ በጎንደር አባል በመሆን ሲታገሉ የኖሩ መሆናቸው ተገልጧል። ይሁን እንጅ ወያኔ አዋጅ አውጆ ነጋሪት ጎስሞ አማራን እንደ ብሔር ለማጥፋት ኢትዮጵያን ደግሞ እንደሀገር ለማፍረስ ጦር ሰብቆ ህዝብ አነቃንቆ በመጣ ጊዜ የመንግስትን የክተት አዋጅ ሳይጠብቁ የዘመቱ ጀግኖች ናቸው። የጎንደር ፋኖ ተነቃንቆ በወጣ ጊዜ በሰሜኑ ጫፍ አዳርቃይ ማይለሃብ ግንባር ከጠላት ጋር ተናንቀው ሀምሌ 16/2013 ዓ/ም በክብር የተሰውት ጀግኖች ስለአማራ ህዝብ ሲሉ የከፈሉት ክቡር መስዋዕትነትና የፈጸሙት ታላቅ ጀብድ ታሪካዊ እና በትውልዱ የሚዘከር ነው። አጽማቸውም በቅርቡ ወደ ትውልድ ቦታቸው መመለሱን ያስታወሰው የአማራ ፋኖ በጎንደር ጥር 20/2015 ዓ/ም ተዝካራቸው በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 በቤተሰቦቻቸው ቤት እንደሚደረግ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አስታውቋል። ከአሚማ ጋር ቆይታ ያደረገው ፋኖ ማቲዎስ እንደገለጸው መላው የአማራ ፋኖ እና በየትኛውም መስመር ውስጥ ሆኖ በአማራ ትግል ላይ የተሰለፈ ሁሉ በዕለቱ በቦታው በመገኘት ጀግኖቹን ነፍስ ይማር እንዲል ጥሪ ቀርቧል። ጥሪውን ያደረጉት የአማራ ፋኖ በጎንደር እና ቤተሰቦቻቸው መሆናቸው ተገልጧል። አድራሻ_ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ሽዋ ዳቦ አካባቢ

Source: Link to the Post

Leave a Reply