የአሸባሪውን ትሕነግ ወረራ በመቀልበስ ረገድ ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ በአዳርቃይ ማይለሃብ ግንባር በክቡር የተሰውት የእነ ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና አዳነ ጎሹ የተዝካር ስነ ስርዓት ወዳጅ ዘመድ፣…

የአሸባሪውን ትሕነግ ወረራ በመቀልበስ ረገድ ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ በአዳርቃይ ማይለሃብ ግንባር በክቡር የተሰውት የእነ ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና አዳነ ጎሹ የተዝካር ስነ ስርዓት ወዳጅ ዘመድ፣ በርካታ የትግል አጋሮቻቸው በተገኙበት ተከናውኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአሸባሪውን ትሕነግ ወረራ በመቀልበስ ረገድ ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ በአዳርቃይ ማይለሃብ ግንባር በክቡር የተሰውት የእነ ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና አዳነ ጎሹ የተዝካር ስነ ስርዓት በርካታ የትግል ጓዶቻቸው እና ተጋባዥ የክብር እንግዶች በተገኙበት ከሰሞኑ መከናወኑ ታውቋል። ፋኖ ሀብቴ ኪዴ እና ፋኖ አዳነ ጎሹ የተባሉ የወንድማማች ልጆች በሁሉም አማራን ከፈፅሞ ጥቃት የመከላከል ትግል ውስጥ ግንባር ቀደም ሆነው የአማራ ፋኖ በጎንደር አባል በመሆን የታገሉ ጀግኖች ናቸው። አማራን ለማጥፋት ብሎም ሀገርን ለማፍረስ መምጣቱን የነገረንን እና መሬት ላይም ይፋዊ ወረራ ላካሄደው የትሕነግ ጦር እጅ አንሰጥም፤ አማራ በወራሪ ሲጠፋ ብሎም ኢትዮጵያ ስትፈርስ ቆመን አናይም በማለት ለአንዲቷ ነፍሳቸው ሳይሰስቱ ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል። በአዳርቃይ ማይለሃብ ሀምሌ 16/2013 ዓ/ም በክብር የተሰውት የእነዚህ ጀግኖች አጽማቸው በቅርብ ጊዜ ወደ ትውልድ አካባቢያቸው እንዲመለስ መደረጉ ይታወሳል። ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመድ፣ የጎንደር ፋኖዎች፣ የክብር እንግዶች በተገኙበት በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ጥር 20/2015 የተዝካር ስነ ስርዓታቸው ተከናውኗል። በእለቱም ሌሎች ከአሁን ቀደም ስለሰፊው የአማራ ህዝብ ብሎም ስለኢትዮጵያ ሲሉ የተሰው ጀግኖችም ተዘክረዋል፤ በትግሉ ከፍ ያለ ሚና የነበራቸው እና አሁንም በትግል ላይ ያሉ ታጋዮችም እንዲታወሱ ተደርጓል። የአማራ ፋኖ በጎንደር እና ቤተሰቦቻቸውም በስፍራው ተገኝተው በተዝካር ስነ ስርዓቱ ለተሳተፉ ወገኖች ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ክብር ስለአማራ ህዝብ ብሎም ስለ ሀገር ሲሉ መስዋዕትነት ለከፈሉ ጀግኖቻችን ሁሉ ይሁን! ለነጻነት ያደረጉት ተጋድሎም በታሪክ እና በትውልድ ዘንድ ሲዘከር ይኖራል!

Source: Link to the Post

Leave a Reply