You are currently viewing የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በጭና እና ቆቦ ንጹሀን ዜጎችን መጨፍጨፉቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች አረጋገጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም       አዲስ አበባ ሸ…

የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በጭና እና ቆቦ ንጹሀን ዜጎችን መጨፍጨፉቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች አረጋገጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸ…

የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በጭና እና ቆቦ ንጹሀን ዜጎችን መጨፍጨፉቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች አረጋገጠ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሂውማን ራይትስ ዎች በአማራ ክልል የተካሄዱ ጭፍጨፋዎችን በተመለከተ ያካሄደውን ምርመራ ሪፖርት ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በጭና እና ቆቦ ከተሞች የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ንጹሀን ዜጎችን ያለርህራሄ መጨፍጨፉቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል። ሂውማን ራይትስ ዎች በዚሁ ሪፖርት ላይ እንዳብራራው፤ ታጣቂዎቹ እእአ ከኦገስት 31 እስከ ሴፕቴምበር 9/2021 ድረስ በአማራ ክልል ንጹሀን ዜጎች በአሸባሪው ታጣቂዎች ተጨፍጭፈዋል። ታጣቂዎቹ እእአ ኦገስት 31/2021ወደ ጭና መግባታቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ በከተማዋ ንጹሀን ሰዎች ያለምንም ምህረት መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል፤ ሂውማን ራይትስ ዎች። በተመሳሳይም እእአ በሴፕቴምበር 9/2021 የአሸባሪው ታጣቂዎች ወደ ቆቦና አካባቢው መግባታቸውን ያስታወሰው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ አሁንም ንጹሀን የሆኑ ዜጎች በተመሳሳይ ያለምንም ምህረት መጨፍጨፋቸውን እንዳረጋገጠ አስታውቋል። ታጣቂዎቹ በእነዚህ አካባቢዎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊቶችን መፈጸማቸውን አረጋግጫለሁ ያለው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ከዓለም አቀፍ የጦር ህግ አንጻርም ከታየ ቡድኑ በቁጥጥሩ ስር የነበሩ ንጹሀን ሰዎችን ያለ ምህረት መጨፍጨፉን በመጥቀስ ድርጊቱ ወንጀል ነው ሲል አስታውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ገለልተኛ አካል በአስቸኳይ ሊያቋቁምና ወንጀሉን ሊመረምር ይገባል ያለው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ በአማራ እና አፋር ክልሎች በእነዚህ ሃይሎች የተፈጸሙ የጦር ወንጀሎችን ሊያጣራና ወንጀለኞችን ተጠያቂ ሊያደርግ ይገባል ሲልም አሳስቧል። ኢፕድ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply