You are currently viewing የአሸባሪው ትሕነግ እና የሱዳን ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ትንኮሳ እንደቀጠለ ነው፤ ላለፉት ተከታታይ ሁለት ቀናት በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ከባድ መሳሪያ እየተኮሱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የአሸባሪው ትሕነግ እና የሱዳን ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ትንኮሳ እንደቀጠለ ነው፤ ላለፉት ተከታታይ ሁለት ቀናት በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ከባድ መሳሪያ እየተኮሱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የአሸባሪው ትሕነግ እና የሱዳን ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ትንኮሳ እንደቀጠለ ነው፤ ላለፉት ተከታታይ ሁለት ቀናት በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ከባድ መሳሪያ እየተኮሱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ትሕነግ እና የሽብር ተባባሪው፣ አሰልጣኝና የመሳሪያ አቅርቦት ክፍሉ ሱዳን በመተማ በኩል ተደጋጋሚ የሚባል ትንኮሳ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። በተለይ ላለፉት 2 ቀናት ህዳር 16 እና 17 ቀን 2014 በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ ጀበል ስኳር አካባቢ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ መዋሉን ነዋሪዎች ለአሚማ ተናግረዋል። ህዳር 17 ቀን 2014 ከቀኑ 4 ሰዓት ጀምሮ በርቀት በከባድ መሳሪያ ሲተኩሱ መዋላቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ በኩል ሁለት ሚሊሾች ቆስለዋል። ህዳር 16 ቀን 2014 ለነበረው የትንኮሳ ተኩስ ምላሽ ያልሰጠችው ኢትዮጵያ ህዳር 17 ቀን 2014 ግን ከርቀት የአጸፋ ምላሽ መስጠቷ ተነግሯል። ጎረቤት ሀገር ሱዳን ትሕነግን ጨምሮ የበርካታ አሸባሪዎችና ሀገር አፍራሾች መሰባሰቢያ ከመሆን አልፋ በስንቅና በትጥቅ ጭምር ድጋፍ በመስጠት ኢትዮጵያ እንድትዳከም እየሰራች መሆኗ ግልጽ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply