የአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ 67 ሰዎችን በግፍ ሲገድሉ 12 ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበ…

የአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ 67 ሰዎችን በግፍ ሲገድሉ 12 ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ታጣቂዎች 67 ሠላማዊ ሰዎችን በግፍ መጨፍጨፋቸውንና 12 ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸውን የዞኑ አስተዳዳር ገልጿል። አሸባሪው ህወሓት ዞኑ በወረራ ይዞ በቆየበት ወቅት 6 ሆስፒታሎችን እና ከ180 በላይ ትምህርት ቤቶችን ማውደሙን እና መዝረፉን የዞኑ አስተዳዳር ጨምሮ ገልጿል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረጻድቅ በሰጡት መግለጫ አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ተቀናጅተው በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ንፁሃንን በግፍ መጨፍጨፋቸውን አመልክተዋል። የህወሓት ወራሪ ኃይል ንፁሃንን ከመጨፍጨፋም ባለፈ የጤና፣ የትምህርትና መሰል ተቋማትና መሰረተ ልማቶችንም አውድሟል ብለዋል። የሰሜን ሸዋ ሕዝብ ከመላ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር አሸባሪዎቹን ከአካባቢው ማስወጣቱን ጠቅሰው፤ በጥቃቱ ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን የማቋቋም ስራ እየተሰራ ገልፀዋል። አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ በሰሜን ሸዋ ዞን አምስት ወረዳዎች ላይ ከፍተውት በነበረው ጥቃት የበርካቶችን ህይወት መቅጠፋቸውን ተናግረዋል። የተጎጂ ቤተሰቦችንና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም በሚደረገው እንቅስቃሴ መላ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ርብርብ እንዲያደርጉ አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply