
የአሸናፊ አካሉ የእስር አድራሻ መታወቁን ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመለከተ፤ ሄደው ለማነጋገር ባይችሉም ከታማኝ ምንጭ አገኘነው ባሉት መረጃ መሰረት አሸናፊ አባይ ማዶ ባለው የልዩ ኃይል ካምፕ ይገኛል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአሸናፊ አካሉን ትክክለኛ የእስር አድራሻ ለማወቅ ተቸግረው የሰነበቱ ቤተሰቦች በማፈላለግ ላይ መሰንበታቸው ይታወቃል። ጥር 7 ቀን 2015 ከቀኑ 10:30 የአድማ ብተና አባላት ባህር ዳር ቀበሌ 14 ከመኖሪያ ቤቱ አፍነው የወሰዱት መሆኑ አይዘነጋም። ጥር 13/2015 ቤተሰብ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት አሸናፊ፣ አባይ ማዶ ባለው የልዩ ኃይል ካምፕ በእስር ላይ ይገኛል። ቤተሰብ ሄዶ ለማነጋገር አልቻለም። ይሁን እንጅ የውስጥ ምንጮች አረጋግጠውልናል በማለት የሰብአዊ መብት ጥሰትም የተፈጸመበት ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
Source: Link to the Post