የአሻራ ሚዲያ ቦርድ አባላት  ለመላው የኢትዮጵያን  ክርስቲያኖች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ ይላል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት  ጌታ ከአምላክነት ሰውነትን መር…

የአሻራ ሚዲያ ቦርድ አባላት ለመላው የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ ይላል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጌታ ከአምላክነት ሰውነትን መር…

የአሻራ ሚዲያ ቦርድ አባላት ለመላው የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ ይላል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጌታ ከአምላክነት ሰውነትን መርጦ ትክክለኛ የሰው ልጅ ባህሪ ምን መምሰል እንዳለበት ያስተማረበት አሀድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጌታ በሰውነቱ መወለዱ ለቀራኒዮው ስቅላት ዳርጎታል፡፡ ውልደቱም ሆነ መሰቀሉም ከዚያም ትንሳዔ ማድረጉ ነፃነትን እስከ መስዕዋትነት የመፈለግ መንገድን ያሳየናል፡፡… የኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ ለኛ ለዚህ ዘመን ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው የሰው ልጅ ከትናንት እስከ ዛሬ ለነበረው እና ላለው አስተማሪ ምሳሌ ይወጣዋል፡፡ ውድ የአሻራ ሚዲያ ደጋፊዎች እና ተከታታዮች ሚዲያችን እውነትን እስከ መስዋዕትነት ዋጋ ከፍሎ ለማውጣት ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ የተደራጀ እንቅስቃሴ እያደረግን መሆናችን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ ነፃነትን መፈለግ፣ እውነትን መግዛት፣ ከተበደሉት ጎን መቆም የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት አስተምሮ ነው፡፡ ይህ አስተምሮ የአሻራ ቦርድ እንደ መልካም አስተምሮ ይወስደዋል፡፡ ወስዶም ለተግባራዊነት ውግናውን ከእውነት ጎን አድርጎ በዮቲዮብ፣ በቴሌግራም፣በፊስቡክ በቅርብ ደግሞ በሳተላይት በቴሌቪዥን መስኮት ወደ እናንተው ቤት ይደርሳል፡፡ ለዚህም ሁሌም ከጎናችችን ሁናችሁ ለደገፋችሁን ሁሉ ላቅ ያለ አክብሮታችንን እገለፅን፣ በዓሉ ለሁሉም የበዓሉ አክባሪዎች ሁሉ የሰላም፣ የተስፋ እና የእውነት እንዲሆንላችሁ የአሻራ ሚዲያ ቦርድ ምኞትን ይገልፃል፡፡ ታህሳስ 28 ቀን፣ 2013 ዓ.ም የአስራት ሚዲያ ቦርድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply